ይነጋል ፡ ይለኛል ፡ ጨለማው (Yenegal Yelegnal Chelemaw) - ኤባ ፡ ድንኤል

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ኤባ ፡ ድንኤል
(Ebba daniel)

Lyrics.jpg


(1)

1
(1)

ቁጥር (Track):

(8)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የኤባ ፡ ድንኤል ፡ አልበሞች
(Albums by Ebba daniel)

ይነጋል ይለኛል ጨለማው
መንጋቱ ላይቀር ሲገባው
ከውድቅት ያለፈ በኔ ባይታይ
ጊዜው እንደደረሰ ነግሮታል ሰማይ
መከራውም ሊያበቃ ስቃዪም ሊሆን ክስተት
ላይመለስ ይሄዳል ጊዜው ሲረፍድበት
መች ዛሬ እንደሚታይ ሁሉ ሊዘልቅበት

 አዝ:- ሊነጋ ሲል ጨለማው ቢበረታም ያቅላላል
ብሩህ ቀን ለማተት ዓይኖቼ ጟጉተዋል (2*)

1.ድፍኑ ቃል ሚስጥሩ ሲገለጥ
ማንም ባይጥር ከፍርዱ ለማምለጥ
እያደረ ነገሩ ሲከፋ
ህይወት ከብዶኝ ቢለኝ ጥፋ ጥፋ
{መከራዬ ከፊቴ ለኔ አይቷል
ሊያልፍ እንዳለ ከሁኔታው አውቋል (2*) }

ይነጋል ይለኛል ጨለማው
መንጋቱ ላይቀር ሲገባው
ከውድቅት ያለፈ በኔ ባይታይ
ጊዜው እንደደረሰ ነግሮታል ሰማይ
መከራውም ሊያበቃ ስቃዪም ሊሆን ክስተት
ላይመለስ ይሄዳል ጊዜው ሲረፍድበት
መች ዛሬ እንደሚታይ ሁሉ ሊዘልቅበት

 አዝ:- ሊነጋ ሲል ጨለማው ቢበረታም ያቅላላል
ብሩህ ቀን ለማተት ዓይኖቼ ጟጉተዋል (2*)

2.ነበር ባልነበር በወረት ሊተካ
እድሜ አለው በቁጥር ሊለካ
መከራዬ ጭንቅ ጣር ያልኩት
ከሞት አልፎ ሲሆን ለህይወት
የምድር ቋጠሮ በሰማይ ሲፈታ
ያመንኩት ለክብሬ ይሆናል ለደስታ
የነፍሴ ቋጠሮ በሰማይ ሊፈታ
አመንኩት ጌታዬን ለዘላለም ደስታ

አዝ:- ሊነጋ ሲል ጨለማው ቢበረታም ያቅላላል
ብሩህ ቀን ለማተት ዓይኖቼ ጟጉተዋል (2*)