ምሥጋናውን (Mesganawen) - ኤባ ፡ ድንኤል

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ኤባ ፡ ድንኤል
(Ebba daniel)

Lyrics.jpg


(1)

1
(1)

ቁጥር (Track):

(5)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የኤባ ፡ ድንኤል ፡ አልበሞች
(Albums by Ebba daniel)

ሰማይ በባርኮቱ ጠሉን ሲያረሰርስ
ምድር አሜን ብሎ በእጥፍ ሲመልስ
ከመለኮት ክብር ሲጠግብ ይህ መንፈሴ
አምልከው አለችኝ በምስጋና ነፍሴ
አክብረው አለችኝ በምስጋና ነፍሴ

አዝ:- ልቤ ያዘጋጀው አለውና
አፌ ተከፈተ እንደገና
የክብር ዙፋኑን የሰራውን
ላዳነው ሊሰዋ ምስጋናውን (2*)
ምስጋናውን ምስጋናውን
በክብር ላለው በሞገስ ላለው
በስልጣን ላለው በክብር ላለው
በዙፋኑ ላለው

በሰው ዘመን ስኖር ስጋ በገዛበት
መንፈሴ የላዪ እንዲያ ቢቀልበት
{የአምልኮ ምዕራፍ በምድር ላይዘጋ
ሰማይ ክበር ሊለው ከልቤ አወጋ (2*)}

አዝ:- ልቤ ያዘጋጀው አለውና
አፌ ተከፈተ እንደገና
የክብር ዙፋኑን የሰራውን
ላዳነው ሊሰዋ ምስጋናውን (2*)
ምስጋናውን ምስጋናውን
በክብር ላለው በሞገስ ላለው
በስልጣን ላለው በክብር ላለው
በዙፋኑ ላለው

ጊዜ ለማይፈታው ለነፍሴ ጥያቄ
በሞት ሲመልሰው ልኖረው አውቄ
{መሰዊያውን ፈቅዶ በልቤ ሲሰራ
ምስጋናውን አፌ ለትውልድ አወራ(2*)}

አዝ:- ልቤ ያዘጋጀው አለውና
አፌ ተከፈተ እንደገና
የክብር ዙፋኑን የሰራውን
ላዳነው ሊሰዋ ምስጋናውን (2*)
ምስጋናውን ምስጋናውን
በክብር ላለው በሞገስ ላለው
በስልጣን ላለው በክብር ላለው
በዙፋኑ ላለው