ማየት ፡ ክርስቶስን (Mayet Kirstosen) - ኤባ ፡ ድንኤል

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ኤባ ፡ ድንኤል
(Ebba daniel)

Lyrics.jpg


(1)

1
(1)

ቁጥር (Track):

(1)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የኤባ ፡ ድንኤል ፡ አልበሞች
(Albums by Ebba daniel)

ማየት ክርስቶስን

አምላክ በሰው አምሳል
በምድር ሲኖር ሳለ
በሀጢያት ሲወቀስ
በሀጢያት መች ዋለ
የህይወት ተምሳሌት
በፅድቅ የኖረውን
እርሱን ብቻ መምሰል
ማየት ክርስቶስን

ማየት ክርስቶስን2*
መኖር ክርስቶስን2*

ሊማር ከህይወት ድካም
ስህተት ካጠለቀ
ዳዊት የልቤ ሰው
ሲባል ከወደቀ
ሊነሳ ይወድቃል ሰው
ሰው በመሆኑ
ፍርዱ ግን ከላይ ነው
የመኖር ተመኑ

አንዱ በሀጢያት አለ
ሌላው ተደብቆ
የሚታየውን ሲዘልፍ
የማይታይ ማን አውቆ
ኖረ ለሞት ብለን
ለሰው ስንሰጥ እርከን
ስለኛ ያለውን ህይወት መች ተረከን
አምላክ በሰው አምሳል
መልካም የመገበኝ ቢቀድመው ስህተቱ
በልቡ የነበረ ሲታይ በድክመቱ
የሰበከውን ባይኖር ያመነውን ረስቶ
ሰው ሊወድ እንዳለ አለ ሊኖር ጠልቶ
አለ ለትውልድ መዳን ሲባል ከረከሰ
ሰው ከፍጥረት ቤቱ ሞትን ከቀመሰ
መፅሀፍ ከፅድቅ በታች
በከንቱ ሁሉን ዘግቶ
አዲስ ምዕራፍ ታየ
መዳን ጌታን አይቶ

ማየት ክርስቶስን2*
መኖር ክርስቶስን2*

ከሰው አድማስ ባሻገር ለክብር ያለውን
እውነት መንገድ ሊሆን ህይወት የኖረውን
የፅድቅን ካባ ለብሶ መዳን ዕለት በዕለት
ማየት እና ማደግ ኢየሱስ ከኖረበት
ማየት እና ማደግ ኢየሱስ ወዳለበት


ማየት ክርስቶስን2*
መኖር ክርስቶስን2*