ልጅነቴ (Lijenete) - ኤባ ፡ ድንኤል

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ኤባ ፡ ድንኤል
(Ebba daniel)

Lyrics.jpg


(1)

1
(1)

ቁጥር (Track):

(6)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የኤባ ፡ ድንኤል ፡ አልበሞች
(Albums by Ebba daniel)

ሌላ ነገር ባይኖር ልጅነቴ በቂ ነው
ለሰማዪ ቤቴ
አዲስ ነገር ባይኖር ደህንነቴ በቂ ነው
ለሰማዪ ቤቴ

ከስጋ ደም ያልሆነ
ክፋይ ከአብራክ ተብሎ
በጥንት የታቀደ መንፈስ የወለደው
ነብስ ደም ተከፍሎ

የሰማዪን ...
ክብር መንግስት
በምድር መኖር ያስጀመረኝ
ሚስጥሩን ተካፋይ
የሀሳቡ ማደሪያ ልጁ አደረገኝ
 
 {መሰረት የሆነኝ ለልጅ ደህንነቴ
በቂ ነው ለእኔ ለሰማዪ ቤቴ} 2*

የሰማዪ ዜጋ ነዋሪ ሆኛለው
ባርነት አይኖርም ልጅ ነህ ተብያለው2*

መሳይ መሳዪን ሊወልድ
ቀድሞ በሀሳብ ፀንሶ
በወሰነው ጊዜ አይኑን በአይኑ ያያል
ስጋ ባህሪውን ለብሶ

 ባህሪ የክርስቶስ ቀደምት እቅዳዊ ዘር
በመስቀል የጣር ሞት
ለነብሴ ማደሪያ ለልጅነት ክብር

{ መሰረት የሆነኝ ለልጅ ደህንነቴ
በቂ ነው ለእኔ ለሰማዪ ቤቴ}

ለምድራዊው ክብር
በእውነት በሀሰት ቢጣር
ያለው እንዳልነበር
ይሆናል ህይወት በሞት ሲሻር

ከሞት በስቲያ አያይም
በምድር እንዲያ ለፍቶ
ያልፋል ላይመለስ
ገንዘብ ሀብቱን ትቶ

ሊኖር የተገባው አንዱ ልጅነቴ
በቂ ነው ለኔ ለሰማዪ ቤቴ 2 *

       ሌላውማ ከንቱ ነው
       ሌላውማ ጠፊ ነው
       የሚታየው በምድር
        ላይታይ ጊዜ አለው