ላንተ ፡ ወይስ ፡ ለሰው (Lante weys le sew) - ኤባ ፡ ድንኤል

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ኤባ ፡ ድንኤል
(Ebba daniel)

Lyrics.jpg


(1)

1
(1)

ቁጥር (Track):

(3)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የኤባ ፡ ድንኤል ፡ አልበሞች
(Albums by Ebba daniel)

የሰጠኸኝን ሳልወድ ከቅርቤ ያለውን ሰው
ያላየሁክን ስመኝ ልቤ ሃሰት አወቀው
አፌ በአምሳልህ ጥላቻን እየቀባ
የሀይማኖት ጦር ሰብቆ በደጄ አደባ

አዝ:- ሃይማኖተኛነቴ ስንቱን እያደማ
ቀና ያልኩት በአንተ እምነተ ጠማማ
ያልሆንኩትን ስሆን ስንቱን ሳስመስለው
ልፋቴ ድካሜ ላንተ ወይስ ለሰው

ለልብሴ ወሮታ ክብር ስም ሰጥቼ
በአእምሮዬ ሰንካላ ንፁህ ሰው ገፍቼ
ላንተ በመሰለኝ ፅፌ በደለዝኩት
መዝገቡ በእኔ ነው በስንቱ የፈረድኩት

አዝ:- ሃይማኖተኛነቴ ስንቱን እያደማ
ቀና ያልኩት በአንተ እምነተ ጠማማ
ያልሆንኩትን ስሆን ስንቱን ሳስመስለው
ልፋቴ ድካሜ ላንተ ወይስ ለሰው

የድርጅት ቀንበር ሆኖብኛል በደም
ማነቆ በእምነቴ ወዳንተ አላደኩም
እጄን ንፁህ ላደርግ በደም እየታጠብኩ
ኖራለሁ በሰው ፊት አለኝ ዘመን እያልኩ

የማደርገውን ይህ ልቤ ያውቃል
ግን የሃይማኖት ዕዳ ይዞኛል
የበግ ለምድ በፊትህ ለብሼ
ክብርህን ቀማሁኝ መልሼ

ሊሻር ባለው ልቤ ታሰረ
ለስርዓቱ ፍቅርን ሰወረ
ኩራቴ ሲቀድመኝ ጥላዬ
መርገሜን ከመርኩት በላዬ
ቆም ብዬ እንዳስብ
ስጠኝ ማስተዋል ጥበብ
በምክርህም ድረስና
ሀይማኖቴን በእምነት አፅና
በምክርህም ድረስና
ዛሬ ልቤን በፍቅርህ አፅና