ጆሮ ፡ ስጠኝ ፡ (Joro setegn) - ኤባ ፡ ድንኤል

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ኤባ ፡ ድንኤል
(Ebba daniel)

Lyrics.jpg


(1)

1
(1)

ቁጥር (Track):

(10)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የኤባ ፡ ድንኤል ፡ አልበሞች
(Albums by Ebba daniel)

አዋጅ ሁሉ ሽብር ሆኖ
መልካም ስራ ፊቴ ባክኖ
ተጠምጄም በሰማሁት
መንታ መንገድ ልቤን ጣልኩት

      ጆሮ ስጠኝ የሚሰማ
      ከመንፈስህ የሚጠማ
      ሰምቶ ልቤን ሚያረጋጋ
      ለጽድቅ ህይወት እንዲተጋ

ውሎ አደረ በመንገድ ሰው በሰማው ሊጠመድ
በምኞቱ ውድቀት ውድቀት ቀድሞት
ካንተ አያደምጥ ጆሮ ክዶት
በየአውታሩ ከፍቶ ወሬ መንፈስህን ቤት ቀብሬ
ጆሮዬ አለ በመንደር ለውድቀቴ ሊቀምር

   ካንተ ሚያደምጥ ለነብሴ ጤና
   ጆሮ ስጠኝ መንፈሴ ይቅና
   ከመልካሙ ምንጭ የሚቀዝፍ
   ቤቴን መርቶ ባንተ የሚያሳርፍ
   ጊዜ አምላኩ የሆነውን ትቶ
   ውስጤ ሊያርፍ ከቃልህ ሰምቶ
   ካንተ ወዳለው የሚፈጥን
    ጆሮ ስጠኝ የሚያደምጥን

       ጆሮ ስጠኝ የሚሰማ
      ከመንፈስህ የሚጠማ
      ሰምቶ ልቤን ሚያረጋጋ
      ለጽድቅ ህይወት እንዲተጋ