ፊትህ ፡ አለ (Fiteh ale) - ኤባ ፡ ድንኤል

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ኤባ ፡ ድንኤል
(Ebba daniel)

Lyrics.jpg


(1)

1
(1)

ቁጥር (Track):

(9)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የኤባ ፡ ድንኤል ፡ አልበሞች
(Albums by Ebba daniel)

አዝ:- ምህረትህ ማለዳ ማለዳ አዲስ ነው
ታማኝነትህም እጅጉን ብዙ ነው
ሰራሁት የምለው በጎነት ሳይኖረኝ
በምህረት በፍቅርህ ዛሬም ምታኖረኝ
አንዳች የሰራሁት ፅድቅ እንኳ ሳይኖረኝ
በመልካምነትህ ዛሬም ምታኖረኝ

1ሁለት ሃሳብ ይዤ በመንታ መንገድ ላይ
ስራመድ እያለሁ ለኔ ያለህን ሳላይ
አንተን በበደልኩት በአእምሮዬ ወቀሳ
ነፍሴ ስትዋዥቅ ስትወድቅ ስትነሳ
ሰራሁ ያልኩት ሲታይ በፋትህ ሲመዘን
ባዶነቴን አየሁ ባለፍኩት ሁሉ ቀን
ጀርባዬን ስሰጥህ ጥላቻን ቋጥሬ
ተመልሼም ባይህ ፊትህ አለ በበሬ

አዝ:- ምህረትህ ማለዳ ማለዳ አዲስ ነው
ታማኝነትህም እጅጉን ብዙ ነው
ሰራሁት የምለው በጎነት ሳይኖረኝ
በምህረት በፍቅርህ ዛሬም ምታኖረኝ
አንዳች የሰራሁት ፅድቅ እንኳ ሳይኖረኝ
በመልካምነትህ ዛሬም ምታኖረኝ

2. ከምሄድበት ከዚያ ከንቱ መውደድ
መልካም ከመሰለኝ በክፉ ስጠመድ
ተመለስ ልጄ ባክህ አይጠቅምም ያ መንገድ
በእኔ ህይወት አለ ከሚያጠፋው ሰደድ
ብሎ የመለሰኝ በምህረት በምክሩ
ደግፎም ይዞኛል ዳግም እንዳልወጣ ከፍቅሩ
መልካምነቶቹ ከፊቴ ሳይጠፉ
መልሶም አኖረኝ ዳግም እንዳልወጣ ከእቅፉ

ፅድቅህ ከልቤ ተስዶ ሸክሜ ከብዶ
ምኞቴን ፀንሼው ሀጢአቴም ሞቴን ወልዶ
እኔም ማረኝ ብዬ ድክመቴን ሳሳየው
ደርሶ በደግ እጁ መርገሜን ሰበረው (2*)

ፊቱ ምንጊዜም የማይለወጥ
በሁኔታዎች ፍቅሩን የማይገልጥ
ከህይወት አምድ ጠፍቼ ካለሁበት ደርሶ
ሆኖኛል ጌታ መርገሜን ፈውሶ
ሆኖኛል አምላክ መንፈሴን ፈውሶ
ሆኖኛል አባት ህይወቴን ፈውሶ