From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
አንተን ፍራ/2 የሚለኝ መንፈስ
የለም ዛሬ ውስጤ አለ በክስ
ኃይልህን ክዶ አመነ ያልኩህ ልቤ
ተቅበዝባዥ ሆንኩ ካንተ ሆኖ አሳቤ X2
በስጋዬ እጣ እድሌ ያልኩት
ሞት ሆነ በብዙ የተመንኩት
ለነፍሴ አተረፍኩ የምለው
በሰማይ ያለኝ ምንድን ነው ?
ባንተ ዘንድ ያለኝ ምንድን ነው?
1. ኖረው በማያውቁት መንግስት ጣታቸውን በላይ ቀሰሩ
አንደበታቸውን በምድር ባንተ ዘበት ሲነጋገሩ
እንደነሱ ብዬ ብናገር እንደሰነፍ ባንተ ባወራ
የደምህን ትውልድ ብበድል ማይገባውን ነገር ብሰራ
በሀጢአት ጥላ ቢያድር ስጋዬ
ደርሶ ቢታይ ቀሎ ዋጋዬ
ተሻገረ ሊያውቅ መንፈሴ
በሰማይ ያለኝን አንዱን ቅርሴ
አዝ:-አብሮነትህ ከቤቴ ራቀ
መንፈሴ ልቤ አለቀ
አምላኬ ባክህ ድረስ
ተስፋዬን ቤቴን /ህይወቴን/ አድስ X2
2. ቢፈልጉት የማያገኙት የሀሳብ ቤት መቼም የማይሰሩት
ህይወት ብለው ለፍተው የኖሩት ቅዠት ሲመስል አምነው የያዙት
በፅድቅ ህይወት ውሎ ማደሩ
እሬት ቢሆን ባንተ ሀሳብ መኖሩ
ቤቴ ሲፈርስ በኃጢአት ሲነዳ
ምን ይባላል ልብ እንኳን ሲከዳ
ብዙ አምላኬ ባንተ ብደክም
ግን ሀሳቤ ካንተ አይለይም
በኑሮዬ ባዶ ብሆንም
ይህ ሀሳቤ ካንተ አይለይም
አብሮነትህ ከቤቴ ራቀ…
|