አዳማዊው ፡ ዕውቀቴ (Adamawiw Ewkete) - ኤባ ፡ ድንኤል

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ኤባ ፡ ድንኤል
(Ebba daniel)

Lyrics.jpg


(1)

1
(1)

ቁጥር (Track):

(2)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የኤባ ፡ ድንኤል ፡ አልበሞች
(Albums by Ebba daniel)

ሰላም ነህ ብዬ ዘምሬ ተናግሬ
ዋይታ ለቅሶ በመንደሬ
አንተ አለኸኝ እያልኩ ባዶነት ሲሰማኝ
ነብሴ ስትጨነቅ ማደርገው አይገባኝ
መልካም ሰራው ብዬ ሲሆንብኝ ጥፋት
በከፋ አስፈርጆኝ የስጋዬ ክፋት
ስል ያዝኩ ከፍታዬን ሳይ ሆኖ ዝቅታ
ከእጄ አለኝ ያልኩት በእልቂት ሲመታ
አንተን ባመንኩት ሲሆንብኝ እረፍት
ከንቱ መረዳቴ አንተን ያወኩበት

 እንዲ ነህ ብዬ ሆነህ ሳላይ
ስታመንብህ ሰልፍ በነብሴ ሳይ
በስምህ ጀምሬ ሳያገኝ ፍፃሜ
በረታው ባንተ ስል ሲፀና ድካሜ

እንዲህ ነህ እንዲያ ነህ ብዬ የለፋውበት*2
አዳማዊዉ እውቀቴ ቀኑ ጨለመበት*2
እንዲህ ነህ እንዲያ ነህ ብዬ የለፋውበት*2
ሰውኛ እውቀቴ ቀኑ ጨለመበት

በመንገዴ ቆመህ ስፀልይ ስገጽጽ በአንደበቴ ላልታነጽ
ሞት መውጊያው በርትቶ በነብሴ ቢያይልም
ባልገቡኝ ነገሮች ለፍርድ ብቸኩልም
አጋጣሚ ምለው ሲያስጨንቁኝ እንዲያ
ነበር አንተ አኑረህ ለስጋዬ መውጊያ

ከፈለከው እንዲያ ውድቀት ድክመቴን
ላንተ በኔ መኖር ካረከው ሞቴን
አፀደኩ ያልኩትን ረገምኩት ልፋቴን
አየው ካንተ ውጪ ከንቱ እኔነቴን
እንዲ ነህ ብዬ ሆነህ ሳላይ
ስታመንብህ ሰልፍ በነብሴ ሳይ
በስምህ ጀምሬ ሳያገኝ ፍፃሜ
በረታው ባንተ ስል ሲፀና ድካሜ

እንዲህ ነህ እንዲያ ነህ ብዬ የለፋውበት*2
አዳማዊዉ እውቀቴ ቀኑ ጨለመበት*2
እንዲህ ነህ እንዲያ ነህ ብዬ የለፋውበት*2
ሰውኛ እውቀቴ ቀኑ ጨለመበት

ከዚ ከንቱ እውቀት ማነው ገላጋዬ
መንፈሴን ታዳጊ አለው አጋዥ ባዬ
የነብሴን ጩኸትስ የቱ ሰው ሊሰማ
አንተ ካልሆንክማ
አንተ ካልሆንክማ