ደክተር ናታን ኦቶሮ(Dr Natan Otoro) (Dr Natan Otoro)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ



የዘላለም መዝናናት ለሞት ቀርበን በታች እንኖር ነበርን ክርስቶስ ባይመጣ ሊያድነን

                  ነገር ግን እሱ አሰበን  ሞታችንን ሞተልን /2

ጸጋው በእምነት አድኖናል

       የክርስቶስ ክቡር ደሙ ዋጅቶናል
               በሞቱ ምክንያት ህይወትን አግኝተናል
     የአንዱ ደም ሁላችንን አንጽቷል
            የጌታ ደም ከኃጢያታችንን  አንጽቷል

ደሙ ነው ያዳነን ደሙ ነው ያነፃን ደሙ ነው ያዳነን ደሙ ነዉ ያነፃን 1. የዘላለምን መዝናናት በጎንም ተስፋ የሰጠን ሞትን ከእኛ ወስዶት አትፍሩ ጌታ አለን

  የዘላለምን መዝናት በጎንም ተስፋ የሰጠን
     የጥሉን ግድግዳ ንዶት ከአብ ጋር አስታረቀን

በእሱ ስራ ሁላችን በአንድ መንፈስ ወደ አብ እንገባለን

     የማዕዘኑ ራስ ድንጋይ ክርስቶስ አድኖናል አሜን

አዝ- ደሙ ነው ያዳነን 2.ለህያዉ ተስፋ ለማይጠፋ እድፈትም ለሌበት

   ሁለተኛ ወለደን  እንደ ምህረቱ ብዛት
            በእሱ ስራ ሁላችን በአንድ መንፈስ ወደ አብ እንገባለን
    የማዕዘኑ ራስ ድንጋይ ክርስቶስ አድኖናል አሜን

አዝ- ደሙ ነው ያዳነን 3. የእምነት ጉዞዋችንን ስንጓዝ ጌታ ብሎናል አይዛችሁ እኔ ህያው ነኝ እናንተ ደግሞ ህያዋን ትሆናላችሁ

   የእምነት ጉዞዋችንን ስንጓዝ ጌታ ብሎናል አይዛችሁ
እስከ አለም ፍጻሜ እናንተ የእኔ ናችሁ
       በእሱ ስራ ሁላችን በአንድ መንፈስ ወደ አብ እንገባለን
         የማዕዘኑ ራስ ድንጋይ ክርስቶስ አድኖናል አሜን

አዝ- ደሙ ነው ያዳነን