ዶ/ር መላኩ ግርማ (Dr Melaku Girma)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

በሰማይና በምድር ፈቃድህ ይከናወናል ሁሉን ልታደርግ ትችላለህ ሃሳብህን ማን ይከለክላል በዓመታት መካከል ስራህን ሁሉ ሰርተሃል አንተ ለዘላለም ጌታ ነህ በክብር ዙፋንህ ጸንተሃል

1/ሃይሌ እጅግ ብዙ ነው ከኔ በላይ ማነው ብሎ የታበየውን ወደ ታች ስትጥለው በቅን ስትፈርድ ስትገልጽ አንተነትህን ከቶ ምን አግዶህ ስታደርግ ፈቃድህን

በሰማይና በምድር ፈቃድህ ይከናወናል ሁሉን ልታደርግ ትችላለህ ሃሳብህን ማን ይከለክላል በዓመታት መካከል ስራህን ሁሉ ሰርተሃል አንተ ለዘላለም ጌታ ነህ በክብር ዙፋንህ ጸንተሃል

2/ሃይልህን ያላወቁ ክንድህን ያልቀመሱ ክብርህን ሊጋፉ በእብሪት የተነሱ መታሰቢያህን ከምድር ሊያስወግዱ የለፉ በቁጣህ እስትንፋስ አለፉ እየጠፉ

በሰማይና በምድር ፈቃድህ ይከናወናል ሁሉን ልታደርግ ትችላለህ ሃሳብህን ማን ይከለክላል በዓመታት መካከል ስራህን ሁሉ ሰርተሃል አንተ ለዘላለም ጌታ ነህ በክብር ዙፋንህ ጸንተሃል

3/ያምላክነትህን የዘለዓለም ሃይል ከጥንትም ጀምሮ በሁሉ ተገልጧል ሥራህ ምስክር ነው ሰወች ቢያስተውሉ ጌታ መሆንህ በፍጥረት በሙሉ

በሰማይና በምድር ፈቃድህ ይከናወናል ሁሉን ልታደርግ ትችላለህ ሃሳብህን ማን ይከለክላል በዓመታት መካከል ስራህን ሁሉ ሰርተሃል አንተ ለዘላለም ጌታ ነህ በክብር ዙፋንህ ጸንተሃል

4/አንተ የከፈትከውን ማነው የሚዘጋ የዘጋኽውንስ ማን ከቶ ይከፍታል ፈቃድህ በሙላት ሁልጊዜ ይሆናል እንደሃሳብህ ላሉት ለበጎ ይፈጸማል