ነፍሴ ፡ ሆይ ፡ አትዘናጊ (Nefsie Hoy Atezanagi) - ደረጀ ፡ ሙላቱ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ደረጀ ፡ ሙላቱ
(Dereje Mulatu)

Lyrics.jpg


(Volume)

ያልታወቀ ፡ አልበም
(Unknown Album)

ቁጥር (Track):

(1)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የደረጀ ፡ ሙላቱ ፡ አልበሞች
(Albums by Dereje Mulatu)

፩) ነቀፋ ፡ ቢበዛ
አጃቢ ፡ ቢታጣ
ያልተጠባበቅነው ፡ መከራ ፡ ቢመጣ
ዕርፉን ፡ ጥለን ፡ አንዴም
ወደ ፡ ሌላም ፡ ሩጫ
የእግዚአብሔር ፡ ሥም ፡ ብቻ
ይሁነን ፡ ማምለጫ
ይህን ፡ ቀን ፡ ነፍሴ ፡ ሆይ!
አትዘናጊ
ቃልኪዳንሽን ፡ ይዘሽ
በእግዚአብሔር ፡ ፊት ፡ ትጊ

አዝ፦ ነፍሴ ፡ ሆይ!
ኢየሱስን ፡ ስንቀበል
ከዚያም ፡ ደግሞ ፡ ለማገልገል
አንቱ ፡ መባል ፡ ሳይጀመር
በረሃው ፡ ላይ ፡ የተባባልነው ፡ ምን ፡ ነበር?

፪) ዝና ፡ ቢበዛልን
ስማችን ፡ ቢወጣ
እልፍ ፡ ገዳይ ፡ ተብሎ
ዘፈንም ፡ ቢመጣ
ሰማይ ፡ ላንቀይር
ማንም ፡ ላይ ፡ ሳንኮራ
በትዕግሥት ፡ እንፈጽም
የእግዚአብሔርን ፡ ሥራ
አንዴም ፡ ነፍሴ ፡ ሆይ!
አትዘናጊ!
ለቃልኪዳንሽ
በእግዚአብሔር ፡ ፊት ፡ ትጊ

አዝ፦ ነፍሴ ፡ ሆይ!
ኢየሱስን ፡ ስንቀበል
ከዚያም ፡ ደግሞ ፡ ለማገልገል
ክብር ፡ ዝናው ፡ ሳይጀመር
ከእግዚአብሔር ፡ ጋር
የተባባልነው ፡ ምን ፡ ነበር?
ከተማ ፡ መግባት ፡ ሳይመጣ
ከእግዚአብሔር ፡ ጋር
የተባባልነው ፡ ምን ፡ ነበር?

፫) መውጊያው ፡ ይነሣልን ፡ ብለን ፡ ስንለምነው
ብሎ ፡ የሚመልስልን
ፀጋዬ ፡ በቂ ፡ ነው
እኛም ፡ እንደ ፡ ጳውሎስ
እንኑር ፡ በጽናት
የእግዚአብሔርን ፡ መንግሥት
በክብር ፡ ልንወርሳት
ነፍሴ ፡ ሆይ!
አትዘግዪ!
ለቃል ፡ ኪዳንሽ
በእግዚአብሔር ፡ ፊት ፡ ትጊ

፬) ዕውነትን ፡ በውሸት ፡ የሚቀላቅሉ
ነጩን ፡ ካድ ፡ አድርገው
ጥቁር ፡ ነው ፡ የሚሉ
ለጥቅም ፡ ያደሩ
ወገኖች ፡ ቢነሡ
እኛ ፡ በታማኝነት
እንኑር ፡ ለንጉሡ
አይደለም ፡ እንዴ!
ነፍሴ ፡ ሆይ
አትዘናጊ!
በፊርማችን
በእግዚአብሔር ፡ ፊት ፡ ትጊ!

አዝ፦ ነፍሴ ፡ ሆይ!
ኢየሱስን ፡ ስንቀበል
ከዚያም ፡ ደግሞ ፡ ለማገልገል
ክብር ፡ ዝናው ፡ ሳይጀመር
ከእግዚአብሔር ፡ ጋር
የተባባልነው ፡ ምን ፡ ነበር?
ክብር ፡ ዝናው ፡ ሳይጀመር
አንቱ ፡ መባል ፡ ሳይጀመር
አገርን ፡ መዞር ፡ ሳይጀመር
ጓዳ ፡ እያለን
ከእግዚአብሔር ፡ ጋር
የተባባልነው ፡ ምን ፡ ነበር?
ከእግዚአብሔር ፡ ጋር
የተገባባነው ፡ ቃል ፡ ኪዳን
ይከበር!