በምርጫ ቀን (# 2 መዝሙር 2 =በምርጫ ቀንTrack 2= Bemircha ken) - ደረጀ ፡ ሙላቱ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ደረጀ ፡ ሙላቱ
(Dereje Mulatu)

Lyrics.jpg


(2)

ያልታወቀ ፡ አልበም
(Unknown Album)

ቁጥር (Track):

(1)

ጸሐፊ (Writer): ግሩም ስንታየሁ
(Girum sintayhu
Property "Writer" has been marked for restricted use.
)
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የደረጀ ፡ ሙላቱ ፡ አልበሞች
(Albums by Dereje Mulatu)

አማራጭን ሁሉ በውሀ ላይ የጣለ
እግዚአብሔር ትዳሬ ኑሮዬ ነው ያለ
ምንጭ አይቶ ያልተጠጋ ለትርፍ ያላደረ
ይታያል ከፊቱ ለእውነት የኖረ

በምርጫ ቀን በውሳኔ ቀን
ማን ምን እንደወሰነ የሚያይ እግዚአብሔር ይመስገን
የዕእማርን ብር ጀግኖች ሲፀየፉ
ሌሎች ግን በስውር በሀሰት ሲዘርፉ
ሰው በእግዚአብሔር ጊዜ የራሱን ቤት ሲያሳምር
 አለ ከላይ የሚያይ ሁሉን ሚመረምር

ፍርስራሹን ጥሎ ማን ማን ኮበለለ
ማንስ በስፍራው ላይ በምድቡ አለ
ማን ወደእርሻ ገባ ማን ለወንጌል ቆመ
ማንስ ምን ዘረፈ ማንስ ምን ጠቀመ
በስራ ቀን በቁርጥ ቀን
ማን የት እንደነበረ የሚያይ እግዚአብሔር ይመስገን

በአገልግሎት ጉዞ ማን ለስራ ወጣ
ማን በር አስከፈተ ብር ወርቅ ሊያመጣ
መሞታችን አይቀር ወይ መነጠቃችን
ያኔ ይከተለናል ስራ ተግባራችን
በአገልግሎት ቀን በግብዣ ቀን
ማን ለምን እንደሄደ የሚያይ እግዚአብሔር ይመስገን

ማን ለቃልህ ጮኸ ማን ለአንደኝነት
ማን ለጥቅም አደረ ማን ተገፋ ለእውነት
ስም ይዞ ማን ተኛ ማን ሆነ እንደስሙ
ሁሉ በመክሊቱ አይቀር መገምገሙ
በአመፅ ቀን በእውነት ቀን
ማን ምን እንዳገለገለ የሚያይ እግዚአብሔር ይመስገን

የገሌ ከእገሌ ይሻላል ይበልጣል
 ያኛውም ከእዛኛው ተግቶ አገልግሏል
ብሎ ሰው ቢመዝን ፍፁም አይደል ውጤቱ
ግን አገዳ እና ወርቁን ያጣራል እሳቱ
በፍርድ ቀን በእሳቱ ቀን
ለሁሉ እንደ ድካሙ የሚሰጥ እግዚአብሔር ይመስገን

ሺ ቢዘመርበት ፆም ፀሎት ቢገባ
ምን ቢነገርበት ቢባርኩት በእምባ
እንክርዳድ ተዘርቶ ስንዴ አይታጨድም
ዘር ላይ ነው መጠንቀቅ ያልተዘራ አይበቅልም

ዝም ያልክ ቀን በትዝብት ቀን ማን ለምን እንደኖረ ምታይ ጌታዬ ተመስገን