ጨመረው (Chemerew) - ደረጀ ፡ ሙላቱ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ደረጀ ፡ ሙላቱ
(Dereje Mulatu)

Lyrics.jpg


(Volume)

ያልታወቀ ፡ አልበም
(Unknown Album)

ቁጥር (Track):

(3)

ርዝመት (Len.): 7:44
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የደረጀ ፡ ሙላቱ ፡ አልበሞች
(Albums by Dereje Mulatu)

ሻለቃ ፡ ሃምሣ ፡ አለቃ
ከፍ ፡ ዝቅ ፡ ቢያደርጉትም
ግድ ፡ የለውም ፡ ዳዊት
አይሞቀው ፡ አይበርደውም
የንጉሥ ፡ ልጅ ፡ ለማግባት
አያገለግልም ፡ (፪X)
ከተማና ፡ ገጠር
ጸባይ ፡ አይቀይረው
ብቻ ፡ እግዚአብሔር ፡ ይክበር
ዳዊት ፡ ደስ ፡ ይለዋል
ያ ፡ መንፈስ ፡ በእኔም ፡ ላይ
ዘርን ፡ ቆጥሮ ፡ መጥቷል {፪X}

ከዘር ፡ ነው
የእግዚአብሔርን ፡ ክብር ፡ አናስነካም
ያልነው ፡ ከዘር ፡ ነው
ከዘር ፡ ነው (፪X)
እንጀራ ፡ ሲጠፋ
ቃልን ፡ በልተን ፡ ያደርነው
ከዘር ፡ ነው
እስቲ ፡ ቁጠሩት ፡ ዘሩን !

የአቋራጩን ፡ ክብር
አሻፈረኝ ፡ ያልነው
ከዘር ፡ ነው
እስቲ ፡ በሉ ፡ ከዘር ፡ ነው
ከእግዚአብሔር ፡ ተወልደን
ከዘር ፡ ነው
የዓመጽ ፡ ግብዣ ፡ ላይ
ጊዜ ፡ የለንም ፡ ያልነው
ከዘር ፡ ነው
ጨመረው ፡ ጨመረው
ዲያብሎስ ፡ ውጊያውን ፡ ጨመረው
ውጊያው ፡ ስለበዛ ፡ የማልቀደስ ፡ መሰለው
ጨመርኩኝ ፡ ጨመርኩኝ ፡ ጨመርኩኝ
ባሰብኝ ፡ ቅድስና
ካቻምናም ፡ በዛ ፡ ምሥጋና
ምሥጋና ፣ ምሥጋና
የሠዋሁት ፡ ለእግዚአብሔር ፡ ምሥጋና
ጠራው ፡ ከእግዚአብሔር ፡ ፊት
የበቀልን ፡ ደመና {፪X}

እዚህ ፡ ቢቆለፍ
እዚያ ፡ ቢዘጋ
ይገኝልኛል ፡ ኑሮ ፡ ቢናጋ
ብሎ ፡ ዲያብሎስ ፡ ቢወድቅ ፡ ቢነሣ
ከከፍታዬ ፡ ነቅነቅ ፡ አልልም
ከዚህ ፡ ከፍታ ፡ በቃ ፡ አልወርድም

አልወርድም ፡ ለሰይጣን ፡ ግብዣ
አልወርድም ፡ በምንም ፡ ዓይነት
አልወርድም ፡ ለሰይጣን ፡ ሃሣብ
አልወርድም ፡ በምንም ፡ ዓይነት
በሰይጣን ፡ ላይ ፡ እሣት ፡ ይውረድበት
አልወርድም ፡ ለሰይጣን ፡ ግብዣ
አልወርድም ፡ ወደ ፡ ርኩሰት
አልወርድም ፡ ኑሮን ፡ ፈርቼ
አልወርድም ፡ በምንም ፡ ዓይነት
በሰይጣን ፡ ላይ ፡ እሣት ፡ ይውረድበት
ሃሌሉያ!

አንዳንዶች ፡ በዓመጽ ፡ በልጽገው
ቢኖሩ ፡ እጅግ ፡ ተቀማጥለው
ለእግዚአብሔር ፡ ኖሬለት ፡ ብደኸይ
እግዚአብሔር ፡ ከእኔ ፡ ጋር ፡ የለም ፡ ወይ?
በቁሳቁስ ፡ ብዛት ፡ ክብሬ ፡ አይመዘንም
ሰይጣን ፡ በመንደሬ ፡ መድረክ ፡ አያገኝም {፪X}

አልሰማም ፡ የሰይጣንን ፡ ስብከት
ጉድለቴን ፡ እያየ ፡ ቢያወራ
በኃጢአት ፡ አንጣላ ፡ እንጂ
ቢያደርግ ፡ ባያደርገው ፡ ቢሠራ ፡ ባይሠራ
ለማንም ፡ አልምልም ፡ አልደራደርም
የሠራዊት ፡ አምላክ ፡ አለ ፡ ከእኔ ፡ ጋራ
አልሰማም ፡ የሰይጣንን ፡ ስብከት
ዙሪያዬ ን፡ እያየ ፡ ቢያወራ
በኃጢአት ፡ አንጣላ ፡ እንጂ
ቢያደርግ ፡ ባያደርገው ፡ ቢሠራ ፡ ባይሠራ
ለማንም ፡ አልምልም ፡ አልደራደርም
የሠራዊት ፡ አምላክ ፡ አለ ፡ ከእኔ ፡ ጋራ

ጨመረው ፡ ጨመረው
ዲያብሎስ ፡ ውጊያውን ፡ ጨመረው
ውጊያው ፡ ስለበዛ ፡ የማልቀደስ ፡ መሰለው
ጨመርኩኝ ፡ ጨመርኩኝ ፡ ጨመርኩኝ
ባሰብኝ ፡ ቅድስና
ካቻምናም ፡ በዛ ፡ ምሥጋና
ምሥጋና ፣ ምሥጋና
የሠዋሁት ፡ ለእግዚአብሔር ፡ ምሥጋና
ጠራው ፡ ከእግዚአብሔር ፡ ፊት
የበቀልን ፡ ደመና {፪X}

አልያዝም! ዛሬም
ድል ፡ የእኔ ፡ ነው
ነገም ፣ ዓርበኛ ፡ ነኝ
ዛሬም ፡ የእግዚአብሔር ፡ ነኝ
ነገም ፡ በኢየሱስ ፡ ያልመጣው
አዲስ ፡ ሰይጣን ፡ የለም
ምንም ፡ አልሆንም
ዛሬም ፡ ሰላሜ ፡ ከኢየሱስ ፡ ነው
ነገም ፡ ድል ፡ የእኔ ፡ ነው
ዛሬም ፡ አልያዝም
ነገም ፡ በኢየሱስ ፡ ያልመጣው
አዲስ ፡ ሰይጣን ፡ የለም
አሜን ፣ አሜን ፣ አሜን ፣ አሜን

ጫፉን ፡ እንዳትነካው
ብሎታል ፡ ጠላቴን
አሜን ፣ አሜን ፣ አሜን ፣ አሜን
ይዘምራል ፡ ሽሸው ፡ ብሎታል ፡ ጠላቴን
አሜን ፣ አሜን ፣ አሜን ፣ አሜን
ጫፉን ፡ እንዳትነካው ፡ ብሎታል ፡ ጠላቴን!
ሃሌሉያ  !