በሞቱ ፡ አዳነኝ (Bemotu Adanegn) - ደረጀ ፡ ሙላቱ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ደረጀ ፡ ሙላቱ
(Dereje Mulatu)

Lyrics.jpg


(1)

ጠቢባኖች
(Tebibanoch)

ቁጥር (Track):

(2)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የደረጀ ፡ ሙላቱ ፡ አልበሞች
(Albums by Dereje Mulatu)

፩) እኔኑ፡ ፍለጋ ፤ ዓመጸኛውን ፡ ሰው
  ተዋረድክ ፡ ኢየሱስ ፡ ክብር ፡ ለሌለው
እኔኑ ፡ ከውርደት ፡ ከማጥ ፡ አወጣኸኝ
ተመስገን ፡ በልፋት ፡በጣር ፡ መጥተህ
ኤሎሄ ፡ ላማሰበቅታኒ ፡ እስክትል ፡ የተሰቃየኸው
ስለእኔ ፡ ሞትህ ፡ ልታድነኝ ፡ በበዛው ፡ የመስቀል ፡ ጣርህ
      ስለእኔ ፡ ለከፈልከው ፡ ዋጋ
      መታሰቢያ ፡ ላድርግ ፡ እስኪ ፡ ዛሬ
      ለመክፈል ፡ ዋጋ ፡ ካሣ ፡ ባይኖረኝም
      ላክብርህ ፡ በፊትህ ፡ ዘምሬ (፪)
እስኪ ፡ አስቡት ፡ ጌታን! አቤቱ!
ማንስ ፡ ይወድህ ፡ ዘንድ? ሃሌሉያ!

  ማንም ፡ እንዲወድህ ፡ ደም ፡ ግባት ፡ የለህም
      የሕማም ፡ ሰው ፡ ነበርክ ፡ ደዌ ፡ ያደቀቀህ
       በመገረፍህ ፡ ቁስል ፡ እኔ ፡ የተፈወስኩት
       በመስቀል ፡ በመሞትህ ፡ከሞት ፡ አመለጥኩኝ ፤
ኤሎሄ ፡ ላማሰበቅታኒ ፡ እስክትል ፡ የተሰቃየኸው
ስለእኔ ፡ ሞትህ ፡ ልታድነኝ ፡ በበዛው ፡ የመስቀል ፡ ጣርህ
      ስለእኔ ፡ ለከፈልከው ፡ ዋጋ
      መታሰቢያ ፡ ላድርግ ፡ እስኪ ፡ ዛሬ
      ለመክፈል ፡ ዋጋ ፡ ካሣ ፡ ባይኖረኝም
      ላክብርህ ፡ በፊትህ ፡ ዘምሬ ፡ ፡ (፪)
እስኪ ፡ የተደረገልንን ፡ እናስባለን!
የቀራንዮን ፡ ፍቅር ፡ እናስባለን!
በመከራ ፡ ሰዓት!

 በመከራ ፡ ሰዓት ፡ በዚያ ፡ ጭንቀትህ
ዓብ ፡ አባትህ ፡ እንኳ ፡ ዝም ፡ አለ ፡ ተወህ
የሁላችን ፡ በቀል ፡ በላይህ ፡ ላይ ፡ ሆነ
በመስቀል ፡ እንዳንተ ፡ የለም ፡ የታመነ

ኤሎሄ ፡ ላማሰበቅታኒ ፡ እስክትል ፡ የተሰቃየኸው ፡
ስለእኔ ፡ ሞትህ ፡ ልታድነኝ ፡ በበዛው ፡ የመስቀል ፡ ጣርህ
      ስለእኔ ፡ ለከፈልከው ፡ ዋጋ
      መታሰቢያ ፡ ላድርግ ፡ እስኪ ፡ ዛሬ
      ለመክፈል ፡ ዋጋ ፡ ካሣ ፡ ባይኖረኝም
      ላክብርህ ፡ በፊትህ ፡ ዘምሬ (፪)
 ሃሌሉያ! ስለእኛ ፡ የታረድክ!
 ለዘላለም ፡ ተባረክ!
የእኛ ፡ ጌታ!

 ልታዘዝህ ፡ ዛሬ ፡ ደስ ፡ ላሰኝህ
ክብርህን ፡ ላያት ፡ ጣርህን ፡ አስቤ
ዋጋ ፡ ከፍለህልኝ ፡ ሰው ፡ አድርገኸኛል
ክበር ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፡ ደምህ ፡ ፈሶልኛል
ኤሎሄ ፡ ላማሰበቅታኒ ፡ እስክትል ፡ የተሰቃየኸው
ስለእኔ ፡ ሞትህ ፡ ልታድነኝ ፡ በበዛው ፡ የመስቀል ፡ ጣርህ
      ስለእኔ ፡ ለከፈልከው ፡ ዋጋ
      መታሰቢያ ፡ ላድርግ ፡ እስኪ ፡ ዛሬ
      ለመክፈል ፡ ዋጋ ፡ ካሣ ፡ ባይኖረኝም
      ላክብርህ ፡ በፊትህ ፡ ዘምሬ (፪x)
ሃሌሉያ!