From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
|
ይህ ፡ ጽሑፍ ፡ ገና ፡ አልተረጋገጠም ። እርማቶች ፡ ሊያስፈልጉት ፡ ይችላል ። ከቻሉ ፡ እርስዎ ፡ ያሻሽሉት ።
|
|
ደረጀ ፡ ሙላቱ (Dereje Mulatu)
|
|
፩ (1)
|
1 (1)
|
ዓ.ም. (Year):
|
2019
|
ቁጥር (Track):
|
፰ (8)
|
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች (Other Songs in the Album)
|
|
የደረጀ ፡ ሙላቱ ፡ አልበሞች (Albums by Dereje Mulatu)
|
|
አራት መቶ ነቢያት እየተነበዩ
ነገስታቶቹ ግን ነቅተው ተወያዩ
አንድ አለ የቀረ ግን ደግ አያወራ
ተብሎ ነብዩ ሚልኪያስ ተጠራ
እግዚሃብሄር ያለውን ሃቁን ነገራቸው
ነገር ሁሉ ሆነ ልክ እርሱ እንዳላቸው
በበላበት ማይጮህ እርሱ ነው እና ደግ
የእግዚሃብሄርን መድረክ ከክፉ እንታደግ
እስኪ እንነጋገር እስኪ እንወያይ
እዚህ ቤት መዋሸት ይፈቀዳል ወይ
እስኪ እንነጋገር እስኪ እንወያይ
አንድ ሲደመር አንድ ሰባት ነው ወይ?
ሰባት ነው ያሉ
ሰባት ነው ያሉ
መድረኮቹን ሞሉ
ሁለት ነው ያሉ
ሁለት ነው ያሉ
አይጋበዙም አሉ
ጌታችን ኢየሱስ የፍቅሩ ጌታ
እውነትን ሲሰብክ በአገልግሎት ቦታ
ትምህርቱ አንዳዶቹን ሲያሰናክላቸው
ለደቀመዛሙርቱ በጣም ከበዳቸው
"ጌታ ሆይ ትምህርትህ ደግ ስላልሆነ፣
ትንሽ ቀየር አድርግው ሰው ተበተነ"
ሲሉት "ከፈለጋችሁ እናንተም ሂዱ" አለ
የእውነት መለኪያ ዛሬስ ወደየት አለ?
እስኪ እንነጋገር እስኪ እንወያይ
እውነት ሰው ቢበትን ልክ አይደለም ወይ?
ይህንን ስዘምር ፊቱ ሚጠቁር ሰው
መጣራት አለበት እርሱ የማን ልጅ ነው?
ጎሰኝነት እና ተንኮል ሰርጎ ገብቶ
ንግድ በእግዚሃብሄር ቤት ገበያ ዘርግቶ
ሳቅ እና ጨዋታ ቀልደኝነት ገኖ
የስኬት መለኪያ የሰው ብዛት ብቻ ሆኖ
ይህ አካሄዳችን ይመርመር የሚሉ
ደግ አይናገሩም ዋናው ፅህፈት ቤት አይምጡ ሲባሉ
ደግ እነማን ናቸው? እስኪ እንወያይ?
የእውነት መለኪያ መፅሃፉ ይታይ
እስኪ እንነጋገር እስኪ እንወያይ
ደረሰኝ መጠየቅ ልክ አይደለም ወይ?
እስኪ እንነጋገር እስኪ እንወያይ
ዋናው ፅህፈት ቤት ኦዲት ይደረጋል ወይ?
እስኪ እንነጋገር እስኪ እንወያይ
ብሔርተኝነት እዚህ በእውነት የለም ወይ?
ጨዋ የለ ባሪያ የለ
ኦሮሞ የለ ሃድያ የለ
አማራ የለ ከምባታ የለ
አንድ አድርጎናል በቀራኒዮ መስቀል ላይ የዋለ
እስኪ እንነጋገር እስኪ እንወያይ
ብሔርተኝነት እዚህ፣ ይፈቀዳል ወይ?
ጨዋ የለ ባሪያ የለ
ሃድያ የለ ትግሬ የለ
አማራ የለ ኦሮሞ የለ
እዚህ የተሰበሰበው አላማው አንድ ነው
ምክኒያቱም ኢየሱስ ለእኛ መስቀል ላይ ስለዋለ
የቤተክርስቲያን አላማው አንድ ነው
የቃለ-ህይወትም አላማው አንድ ነው
ወንጌልን ለፍጥረት መስበክን ብቻ ነው
ከዚህ ውጪ ድብቅ አጀንዳ ያላችሁ
ቸርቿን እንድትለቁ ትጠየቃላችሁ
የትውልድን እድሜ ገንዘብ እየበሉ
በጣፋጭ ንግግር ጊዜ እየገደሉ
ቁስል እያከኩ ለውጥ የማያመጡ
ወይ የማይመልሱ ወይ የማየለውጡ
ደግሞ እውነት አፍርጠው ሚና ለዩ ሚሉ
ተወደው ለመኖር ትውልድ የማይገድሉ
እነማን ናቸው ደግ ለወንጌል ያደሩ
ስብሰባ እንቀመጥ ሁሉም ይመርመሩ
ጥሪ ያላቸው ይቀመጡ
ያልተጠሩ ይባረሩ
|