From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
አዝ፦ በምሥራቅ ፡ በምዕራብ ፡ በሰሜን ፡ በደቡብ
የተበታተኑት ፡ ይሰበሰባሉ
በአንድ ፡ ጣራ ፡ ሥር ፡ ሆነው ፡ ዳግመኛ ፡ ጌታን ፡ ያከብራሉ (፪x)
አሁን ፡ የጨለመ ፡ መስሎ ፡ ብታየንም
ወጋገን ፡ ይወጣል ፡ ልናይ ፡ ሁሉንም
የገነባው ፡ ጠላት ፡ ነፋፍቶ ፡ ደረቱን
እግዚአብሔር ፡ በቃ ፡ ስል ፡ ይለቃል ፡ መንገዱን (፪x)
አዝ፦ በምሥራቅ ፡ በምዕራብ ፡ በሰሜን ፡ በደቡብ
የተበታተኑት ፡ ይሰበሰባሉ
በአንድ ፡ ጣራ ፡ ሥር ፡ ሆነው ፡ ዳግመኛ ፡ ጌታን ፡ ያከብራሉ (፪x)
በስቃይ ፡ በሀዘን ፡ የተበተኑቱ
በአንድ ፡ ልከማቹ ፡ ተቃርቧል ፡ ሰዓቱ
ሥሙን ፡ ልያስከብር ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ ተንቀሳቅሷል
የልጆቹን ፡ ፀሎት ፡ ከፀበዖት ፡ ሰምቷል
አዝ፦ በምሥራቅ ፡ በምዕራብ ፡ በሰሜን ፡ በደቡብ
የተበታተኑት ፡ ይሰበሰባሉ
በአንድ ፡ ጣራ ፡ ሥር ፡ ሆነው ፡ ዳግመኛ ፡ ጌታን ፡ ያከብራሉ (፪x)
ቀን ፡ እንቆጥራለን ፡ አንድ ፡ ሁሉት ፡ ብለን
ጌታ ፡ በደጅ ፡ ነው ፡ ካሳውን ፡ ልክሰን
ከአራቱም ፡ ማዕዘን ፡ ክርቲያኖች ሁሉ
በምድራቸው ፡ ጌታን ፡ ዳግም ፡ ያከብራሉ
አዝ፦ በምሥራቅ ፡ በምዕራብ ፡ በሰሜን ፡ በደቡብ
የተበታተኑት ፡ ይሰበሰባሉ
በአንድ ፡ ጣራ ፡ ሥር ፡ ሆነው ፡ ዳግመኛ ፡ ጌታን ፡ ያከብራሉ (፪x)
|