ይቅርታን ፡ ለማድረግ (Yeqertan Lemadreg) - ደረጀ ፡ ከበደ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ደረጀ ፡ ከበደ
(Dereje Kebede)

Dereje Kebede 6.png


(6)

ዝም ፡ አልልም
(Zem Alelem)

ቁጥር (Track):

(8)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የደረጀ ፡ ከበደ ፡ አልበሞች
(Albums by Dereje Kebede)

ምህረትህ ፡ በእኔ ፡ ላይ ፡ እንድሆን ፡ እሻለሁ
እኔ ፡ ግን ፡ በቀልን ፡ ወዳጅ ፡ አድርግያለሁ
ነፍሴ ፡ ተጎሳቁላ ፡ ፍጹም ፡ ሳያምርባት
ተኮንና ፡ እንዳትኖር ፡ ይቅርታን ፡ አስተምራት

አዝ፦ ይቅርታን ፡ ለማድረግ ፡ ልቤ ፡ አልሆን ፡ እያለው
እግሬ ፡ የሚራመደው ፡ ሸካራ ፡ መንገድ ፡ ነው
የእግዚአብሔር ፡ ልጅ ፡ ሆይ ፡ ድካሜን ፡ ታውቃለህ
ዳብሰኝ ፡ እንደገና ፡ ትለውጠኛለህ

ወንድሜን ፡ ማቁሰሌ ፡ እጅግ ፡ ይረሳኛል
የተበደልኩትን ፡ መቁጠር ፡ ይጥመኛል
ምን ፡ አለበት ፡ ዛሬ ፡ ልቤን ፡ ብትጠርበው
መቀጥቀጫው ፡ ብረት ፡ መዶሻው ፡ በእጅህ ፡ ነው

አዝ፦ ይቅርታን ፡ ለማድረግ ፡ ልቤ ፡ አልሆን ፡ እያለው
እግሬ ፡ የሚራመደው ፡ ሸካራ ፡ መንገድ ፡ ነው
የእግዚአብሔር ፡ ልጅ ፡ ሆይ ፡ ድካሜን ፡ ታውቃለህ
ዳብሰኝ ፡ እንደገና ፡ ትለውጠኛለህ

እጄን ፡ ለአንተ ፡ ሰጠው ፡ አንተ ፡ እንድታስተምረኝ
ለውጠኝ ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ይሄው ፡ በፊትህ ፡ ነኝ
የበደለኝን ፡ ሰው ፡ ይቅር ፡ ብዬ ፡ እንዳልፈው
በቀልን ፡ ሳላስብ ፡ በፍቅር ፡ እንዳቅፈው

አዝ፦ ይቅርታን ፡ ለማድረግ ፡ ልቤ ፡ አልሆን ፡ እያለው
እግሬ ፡ የሚራመደው ፡ ሸካራ ፡ መንገድ ፡ ነው
የእግዚአብሔር ፡ ልጅ ፡ ሆይ ፡ ድካሜን ፡ ታውቃለህ
ዳብሰኝ ፡ እንደገና ፡ ትለውጠኛለህ

ምህረትህ ፡ በእኔ ፡ ላይ ፡ እንድሆን ፡ እሻለሁ
እኔ ፡ ግን ፡ በቀልን ፡ ወዳጅ ፡ አድርግያለሁ
ነፍሴ ፡ ተጎሳቁላ ፡ ፍጹም ፡ ሳያምርባት
ተኮንና ፡ እንዳትኖር ፡ ይቅርታን ፡ አስተምራት