ወረት ፡ አያውቀው ፡ ጌታዬ (Weret Ayawqew Gietayie) - ደረጀ ፡ ከበደ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ደረጀ ፡ ከበደ
(Dereje Kebede)

Dereje Kebede 6.png


(6)

ዝም ፡ አልልም
(Zem Alelem)

ቁጥር (Track):

(1)

ርዝመት (Len.): 4:44
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የደረጀ ፡ ከበደ ፡ አልበሞች
(Albums by Dereje Kebede)

ወረት ፡ አያውቀው ፡ ጌታዬ
 ዘላለም ፡ ሚስጥረኛዬ
 የልቤን ፡ አጫውተዋለሁ
 ገበናዬን ፡ አሳየዋለው(x፪)

 ለሰው ፡ ብመስል ፡ የደላኝ
 ውስጤ ፡ ግን ፡ እሳት ፡ ንዳድ ፡ ነዉ
 አፌን ፡ አልከፍትም ፡ ለማንም
 ጌታ ፡ ያውቀዋል ፡ ትርፌን ፡ ጉድለቴንም(x፪)

 ወረት ፡ አያውቀው ፡ ጌታዬ
 ዘላለም ፡ ሚስጥረኛዬ
 የልቤን ፡ አጫውተዋለሁ
 ገበናዬን ፡ አሳየዋለው(x፪)

 ዝክዝክ ፡ አድርጌ ፡ ሚስጥሬን
 አስጸያፊውን ፡ ስራዬን
 እነግረዋለሁ ፡ ታማኝ ፡ ነው
 ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ጊዜ ፡ የማይለውጠው(x፪)

 ወረት ፡ አያውቀው ፡ ጌታዬ
 ዘላለም ፡ ሚስጥረኛዬ
 የልቤን ፡ አጫውተዋለሁ
 ገበናዬን ፡ አሳየዋለው(x፪)

 ሳዝን ፡ ስተክዝ ፡ በኑሮ
 አሰማዋለው ፡ እሮሮ
 ብቸኝነቴ ፡ ሲያርደኝ
 በእየሱስ ፡ መጽናናት ፡ አለኝ(x፪)

 ወረት ፡ አያውቀው ፡ ጌታዬ
 ዘላለም ፡ ሚስጥረኛዬ
 የልቤን ፡ አጫውተዋለሁ
 ገበናዬን ፡ አሳየዋለው(x፪)

 አላምናቸው ፡ ወላጆቼን
 ጓደኛዎች ፡ ዘመዶቼን
 ያጋልጡኛል ፡ ጠብቀው
 አይችሉትም ፡ ጉዴን ፡ ተሸክመው(x፪)

 ወረት ፡ አያውቀው ፡ ጌታዬ
 ዘላለም ፡ ሚስጥረኛዬ
 የልቤን ፡ አጫውተዋለሁ
 ገበናዬን ፡ አሳየዋለው(x፪)

 ወረት ፡ አያውቀው ፡ ጌታዬ
 ዘላለም ፡ ሚስጥረኛዬ
 የልቤን ፡ አጫውተዋለሁ
 ገበናዬን ፡ አሳየዋለው(x፫)