From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
ሕይወት በሰላሙ ምንኛ ይጥማል
እግዚአብሔር ቅርብ ነው ጸሎትም ይሰማል
የፈለጉት ሲሆን ደጅ ቤት ሲሞላ
ክርስትና ግሩም ግሩም እንደ ሌላ
አዝ፡- መከራ ሳይመጣ ሁሉም ክርስቲያን ነው
ሁል ጊዜ ሀሌሉያ ከአፉ ማይለየው
መበጠር ሲከሰት ሁሉም ይሸበራል
ጠመንጃው ጥይቱ ከእጁ ይሽቀነጠራል
ገለባው ከስንዴው መለየት ሲጀምር
አስመሳይ ሲሯሯጥ ይታያል ግርግር
ሀሳዊው ሰባኪ ከመድረክ ይሮጣል
ዘማሪው ደብተሩን ጉያው ይደብቃል
አዝ፡- መከራ ሳይመጣ ሁሉም ክርስቲያን ነው
ሁል ጊዜ ሀሌሉያ ከአፉ ማይለየው
መበጠር ሲከሰት ሁሉም ይሸበራል
ጠመንጃው ጥይቱ ከእጁ ይሽቀነጠራል
ያ ግን ያምላክ ወዳጅ ኢየሱስን ያውቃል
አታላይ ሲገለጥ ቀስቱን ይደግናል
እሳቱን ባህሩን ታግሶ ተሸግሮ
ጌታን ይገናኛል ክብር ተሸልሞ
አዝ፡- መከራ ሳይመጣ ሁሉም ክርስቲያን ነው
ሁል ጊዜ ሀሌሉያ ከአፉ ማይለየው
መበጠር ሲከሰት ሁሉም ይሸበራል
ጠመንጃው ጥይቱ ከእጁ ይሽቀነጠራል
|