From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
ለረጅም ፡ ዘመናት ፡ ተቆልፎባቸው ፡ ኤሄሄ ፡ ኤሄሄ ፡ ኤሄዉ
የፈርዖን ፡ ሠራዊት ፡ የሚያንገላታቸው
አሉ ፡ የተገፉ ፡ ስምን ፡ ለማስከበር ፡ ኤሄሄ ፡ ኤሄሄ ፡ ኤሄዉ
ጌታ ፡ ሆይ ፡ ገርስሰው ፡ የጠላትን ፡ መንደር (፪x)
አዝ፦ ስለ ፡ ሥምህ ፡ ተጠልተው ፡ ያሉትን ፡ በሰንሰለት (፪x)
አብራላቸው ፡ ክብርህን ፡ ጋርዳቸው ፡ ከመታከት
ግንባራቸው ፡ ይጠንክር ፡ ጠላታቸው ፡ ይርበትበት
ለሥምህ ፡ ነዉና ፡ ልጆችህን ፡ አጽና
አንተን ፡ እንድክዱ ፡ ባንተ ፡ እንዲያማሪሩ ፡ ኡሁሁ ፡ ኡሁሁ ፡ ኡሁዉ
ይሸርባል ፡ ጠላት ፡ ብዙ ፡ ነው ፡ ምስጥሩ
ምርት ፡ በሕይወታቸው ፡ እንዳይሆን ፡ ጋርዳቸው ፡ ኤሄሄ ፡ ኤሄሄ ፡ ኤሄው
ፈቃድህ ፡ ይፈፀም ፡ እንድትከብርባቸው (፪x)
አዝ፦ ስለ ፡ ሥምህ ፡ ተጠልተው ፡ ያሉትን ፡ በሰንሰለት (፪x)
አብራላቸው ፡ ክብርህን ፡ ጋርዳቸው ፡ ከመታከት
ግንባራቸው ፡ ይጠንክር ፡ ጠላታቸው ፡ ይርበትበት
ለሥምህ ፡ ነዉና ፡ ልጆችህን ፡ አጽና
ጠላትም ፡ ይንቀጥቀጥ ፡ ይታሰር ፡ ምላሱ ፡ ኡሁሁ ፡ ኡሁሁ ፡ ኡሁዉ
ይተብተብ ፡ እጅ ፡ እግሩ ፡ ይቅር ፡ መላወሱ
ፍጥረት ፡ ሁሉ ፡ ይመስክር ፡ ስለ ፡ ኃያልነት ፡ እሂሂ ፡ እሂሂ ፡ እሂ
ይሳቁ ፡ በፈርዖን ፡ ድል ፡ ያርጉ ፡ ልጆችህ (፪x)
አዝ፦ ስለ ፡ ሥምህ ፡ ተጠልተው ፡ ያሉትን ፡ በሰንሰለት (፪x)
አብራላቸው ፡ ክብርህን ፡ ጋርዳቸው ፡ ከመታከት
ግንባራቸው ፡ ይጠንክር ፡ ጠላታቸው ፡ ይርበትበት
ለሥምህ ፡ ነዉና ፡ ልጆችህን ፡ አጽና
ከእንግድህ ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ፀሎታችን ፡ ስማ ፡ አሀሀ ፡ አሀሀ ፡ አሀ
ታምነናል ፡ በኃይልህ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ አንተማ
እንክትክት ፡ ብለዉ ፡ የወይንህ ፡ መዝጊያዎ ፡ ኦሆሆ ፡ ኦሆሆ ፡ ኦሆች
ያምልኩሁል ፡ በክብር ፡ በድል ፡ ያንተ ፡ ልጆችህ (፪x)
አዝ፦ ስለ ፡ ሥምህ ፡ ተጠልተው ፡ ያሉትን ፡ በሰንሰለት (፪x)
አብራላቸው ፡ ክብርህን ፡ ጋርዳቸው ፡ ከመታከት
ግንባራቸው ፡ ይጠንክር ፡ ጠላታቸው ፡ ይርበትበት
ለሥምህ ፡ ነዉና ፡ ልጆችህን ፡ አጽና (፪x)
|