ጭንቀቴን ፡ ላዋየው (Chenqetien Lawayew) - ደረጀ ፡ ከበደ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ደረጀ ፡ ከበደ
(Dereje Kebede)

Dereje Kebede 6.png


(6)

ዝም ፡ አልልም
(Zem Alelem)

ቁጥር (Track):

(10)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የደረጀ ፡ ከበደ ፡ አልበሞች
(Albums by Dereje Kebede)

አዝ፦ ማለዳ ፡ ስነሳ ፡ ጭንቀተን ፡ ላዋይህ
ነፍሴን ፡ ያዛላትን ፡ ችግሬን ፡ ላሳይህ
ግራ ፡ ቀኝም ፡ አልልም ፡ ምስጥረኛም ፡ የለኝ
ኢየሱስ ፡ ፈጥነህ ፡ ናና ፡ ከሀዘኔ ፡ ገላግልኝ (፪x)

ምነው ፡ መጨነቄ ፡ ረዳት ፡ እንደሌለው
አሕዛብ ፡ ያውቃሉ ፡ በአንተ ፡ እቅፍ ፡ እንዳለሁ
አጥፍቼም ፡ እንደሆን ፡ ቅጣኝ ፡ እንደ ፡ ልጅህ
የለፋህብኝ ፡ ነኝ ፡ ፈሶልኛል ፡ ደምህ (፪x)

አዝ፦ ማለዳ ፡ ስነሳ ፡ ጭንቀተን ፡ ላዋይህ
ነፍሴን ፡ ያዛላትን ፡ ችግሬን ፡ ላሳይህ
ግራ ፡ ቀኝም ፡ አልልም ፡ ምስጥረኛም ፡ የለኝ
ኢየሱስ ፡ ፈጥነህ ፡ ናና ፡ ከሀዘኔ ፡ ገላግልኝ (፪x)

በዓይን ፡ የማይታዩ ፡ ሠራዊቶች ፡ አሉኝ
ጠላቴን ፡ ከእግሬ ፡ ሥር ፡ የሚያንጋልሉልኝ
ብዬ ፡ ተናግሬ ፡ ለዓለም ፡ ዙሪያ ፡ ሁሉ
አሁን ፡ ብንቀጠቀጥ ፡ ታድያ ፡ ምን ፡ ይላሉ (፪x)

አዝ፦ ማለዳ ፡ ስነሳ ፡ ጭንቀተን ፡ ላዋይህ
ነፍሴን ፡ ያዛላትን ፡ ችግሬን ፡ ላሳይህ
ግራ ፡ ቀኝም ፡ አልልም ፡ ምስጥረኛም ፡ የለኝ
ኢየሱስ ፡ ፈጥነህ ፡ ናና ፡ ከሀዘኔ ፡ ገላግልኝ (፪x)

ጉድለቱን ፡ አውቃለሁ ፡ እኔው ፡ ነኝ ፡ ምክንያቱ
ለስጋም ፡ ለነፍሴም ፡ እሾህ ፡ የሆንኩቱ
አንተ ፡ ግን ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ምህረት ፡ የተሞላህ
ጠግነኝ ፡ በቁጣህ ፡ አስተምረኝ ፡ እንዳሻህ

አዝ፦ ማለዳ ፡ ስነሳ ፡ ጭንቀተን ፡ ላዋይህ
ነፍሴን ፡ ያዛላትን ፡ ችግሬን ፡ ላሳይህ
ግራ ፡ ቀኝም ፡ አልልም ፡ ምስጥረኛም ፡ የለኝ
ኢየሱስ ፡ ፈጥነህ ፡ ናና ፡ ከሀዘኔ ፡ ገላግልኝ (፪x)