ዓለምን ፡ እንዳላይ (Alemen Endalay) - ደረጀ ፡ ከበደ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ደረጀ ፡ ከበደ
(Dereje Kebede)

Dereje Kebede 6.png


(6)

አልበም
(Dereje 6)

ቁጥር (Track):

፲ ፪ (12)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የደረጀ ፡ ከበደ ፡ አልበሞች
(Albums by Dereje Kebede)

አለምን እንዳላይ አይኔን ተቆጣጠር
ቀስ በቀስ እንዳልሄድ ወደ አታላይ ሃገር
አንተ ብቻ እንድትሆን ማርና ወተቴ
በእግርህ ስር እንድኖር ይሄ ነው ፀሎቴ

ዝናም ከበሬታም ይጠፋሉ ፈጥነው
አይደለም ነዋሪ ሃብትም እንደ ጢስ ነው
ዘለአለም ነዋሪ ኢየሱስ ብቻ ነው

መንፈሳዊ አይኖቼን ክፈታቸውና
ልመልከት ጌታ ሆይ ደጉን እንደገና
የጥንቱን ፍቅሬን ዳግም ብታለብሰኝ
አያለሁ አጥርቼ ጉምም አይሸፍነኝ

ዝናም ከበሬታም ይጠፋሉ ፈጥነው
አይደለም ነዋሪ ሃብትም እንደ ጢስ ነው
ዘለአለም ዘላቂ ኢየሱስ ብቻ ነው

አተርፍ ባይ አጉዳይ መሆን ያስፈራኛል
ከአንተ ጋር መሆኑ እጅግ ያዋጣኛል
ህይወት መች ይሰጣል ወርቅ ቢያብረቀርቅ
ቅብዝብዝ ይሆናል ሰው ከአንተ ቤት ሲርቅ

ዝናም ከበሬታም ይጠፋሉ ፈጥነው
አይደለም ነዋሪ ሃብትም እንደ ጢስ ነው
ዘለአለም ዘላቂ ኢየሱስ ብቻ ነው

የሰጠኅኝን ግብ እንዳልጥለው ወዲያ
እንዳልገባ ሲኦል ከህይወት በስቲያ
ይቅርብኝ እንግዲህ ብናኙ ግሳንግስ
ልኑር በአንተ ጥላ ልቤን ለአንተ ላፍስስ

ዝናም ከበሬታም ይጠፋሉ ፈጥነው
አይደለም ነዋሪ ሃብትም እንደ ጢስ ነው
ዘለአለም ነዋሪ ኢየሱስ ብቻ ነው