የዛሬ ፡ ቤተክርስቲያን (Yezarie Bietekerestiyan) - ደረጀ ፡ ከበደ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ደረጀ ፡ ከበደ
(Dereje Kebede)

Dereje Kebede 9.jpg


(9)

የአድናቆት ፡ ቀን ፡ ለእግዚአብሔር
(Yeadnaqot Qen LeEgziabhier)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፪ (2010)
ቁጥር (Track):

(7)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የደረጀ ፡ ከበደ ፡ አልበሞች
(Albums by Dereje Kebede)

በቀድሞው ፡ ስብስብ ፡ በአዲስ ፡ ኪዳን ፡ ህብረት
ምዕመናን ፡ አብረው ፡ በተከማቹበት
ንብረቱን ፡ ገንዘቡን ፡ ሁሉን ፡ እያመጣ
ማንም ፡ ሳይራቆት ፡ እንጀራም ፡ ሳያጣ
በአንድ ፡ ልብ ፡ ጌታን ፡ እያመሰገኑ
ይቆርሱ ፡ ነበረ ፡ ያኔ ፡ ምዕመኑ
ህብረት ፡ እንድናደርግ ፡ ያስተማረን ፡ ቃሉ
እንዲህ ፡ ዓይነት ፡ ነበር ፡ ምዕመን ፡ አስተውሉ

ዛሬ ፡ ቤተክርስቲያን ፡ እያሉ ፡ የሚጠሩት
በየጐዳናው ፡ ላይ ፡ አስጊጠው ፡ የሰሩት
አናጢ ፡ የዋለበት ፡ ከመሰረት ፡ ከላይ
በቁመት ፡ በስፋት ፡ ባሻገር ፡ የሚታይ
ለዓይን ፡ ጥጋብ ፡ እንጂ ፡ ሕይወት ፡ የሌለበት
ያዘነ ፡ የራበው ፡ ደጅ ፡ የሚቆምበት
የነፍሳት ፡ ጥሪ ፡ ስብከቱ ፡ ተረስቶ
እቁብ ፡ መሰብሰቢያ ፡ ሰው ፡ ጌታ ፡ ቤት ፡ መጥቶ

የአዲስ ፡ ኪዳን ፡ ህብረት ፡ የሃዋሪያቱ
በአንድ ፡ ልብ ፡ ሁሉም ፡ የቆረሱበቱ
ሁሉም ፡ የኢየሱስ ፡ ሥም ፡ በልብ ፡ በአንደበቱ
በዚህ ፡ ዘመን ፡ ይሁን ፡ አሜን ፡ ይሁን ፡ በሉ
ያ ፡ ነው ፡ የእኔ ፡ ጸሎት ፡ ለቅዱሳን ፡ ሁሉ

ሰንበት ፡ ጠብቆ ፡ እንዲያው ፡ ለወጉ
መሰባሰቡ ፡ ደንቡን ፡ ማድረጉ
ያለክርስቶስ ፡ ኦና ፡ ነው ፡ ቤቱ
ጭፈራው ፡ አጉል ፡ ዝማሬው ፡ ከንቱ

የዛሬው ፡ ቤተክርስቲያን ፡ ባለአስር ፡ ሺህ ፡ አባላት
የቁጥር ፡ እሽቅድምድም ፡ የአባል ፡ ቅጽ ፡ ሙላት
መቶ ፡ የነበረው ፡ በሺህ ፡ እንዲቆጠር
ማን ፡ ይበልጥ ፡ በብዛት ፡ ብሎ ፡ መፎካከር
ህዝቡ ፡ ተጠራቅሞ ፡ አዳራሽ ፡ ይጠባል
ሰው ፡ ሰውን ፡ አያውቀው ፡ ይገባል ፡ ይወጣል
የዛሬው ፡ እረኛ ፡ አባላት ፡ ይቆጠራል
ለጋስና ፡ ሃብታሙን ፡ ለማግኘት ፡ ይጥራል

የሥም ፡ ቤተክርስቲያን ፡ ሞልቷል ፡ በየጓሮው
ገብተው ፡ ለሚያዩት ፡ ግን ፡ ውስጡ ፡ ግን ፡ ሌላ ፡ ነው
መሪዎች ፡ ተብለው ፡ የሚያስተዳድሩ
እንደ ፡ ጳውሎስ ፡ መስራት ፡ ሰንፈው ፡ ያልተማሩ
ሰርተው ፡ የማያውቁ ፡ ወንበር ፡ የሚያሞቁ
በላብ ፡ የማግኘትን ፡ ሚስጥር ፡ የማያውቁ
በስልጣን ፡ በገንዘብ ፡ እርስ ፡ በርስ ፡ ጡጫ
እግዚአብሔር ፡ በእነርሱ ፡ የዓለም ፡ ማላገጫ

በየእሁዱ ፡ ጉባኤው ፡ ስጡ ፡ ስጡ ፡ ሰፍኖ
ከሃብታም ፡ ከደሃው ፡ ብር ፡ ተለምኖ
ቀድሞ ፡ ከተሰሩት ፡ አብልጥ ፡ የሚያኮራ
ባልሚሊዮን ፡ ብር ፡ አዳራሽ ፡ ሊሰራ
የእገሌ ፡ ቤተክርስቴን ፡ እጹብ ፡ ድንቅ ፡ ስራ
የሰው ፡ ልጅ ፡ የራሱን ፡ ስሙን ፡ እንዲያስጠራ
ባዶ ፡ ሆድ ፡ የመጡ ፡ የራባቸው ፡ ሁሉ
ለአዳራሹ ፡ መስሪያ ፡ ስጡ ፡ ይባላሉ

በሰንበቱ ፡ ህብረት ፡ ግራ ፡ ቀኝ ፡ ላየ ፡ ሰው
አለ ፡ በጌታ ፡ ቤት ፡ ያጣ ፡ የሚቆርሰው
ሱሪው ፡ የተጣፈ ፡ መጫሚያው ፡ ያለቀ
መቆም ፡ የተሳነው ፡ አቅሙ ፡ የደቀቀ
ሞልቷል ፡ ውስጡ ፡ የሚጮህ ፡ በጌታ ፡ ፊት ፡ ወድቆ
የእግዚአብሔር ፡ ገንዘብ ፡ ግን ፡ ባንክ ፡ ተጨናንቆ
ስስታም ፡ መሪዎች ፡ ያው ፡ ሲስገበገቡ
የመንግስት ፡ ሲሳይ ፡ አይቀርም ፡ መሆኑ

በእግዚአብሔር ፡ ቤት ፡ በረከት ፡ ይብዛ
መብል ፡ ይሁን ፡ ለራበው ፡ በዛ
የሳጥኑን ፡ ቁልፍ ፡ የያዛችሁ
የጌታን ፡ ገንዘብ ፡ ጉዋዳ ፡ ያሸሻችሁ
ሰማይ ፡ ጫፍ ፡ ደርሶዋል ፡ መሰሰታችሁ
ለራበው ፡ ለጠማው ፡ በትኑት ፡ አውጡና
የእግዚአብሔርን ፡ ገንዘብ ፡ ማካበት ፡ ይቅርና