የሰው ፡ አስታማሚ (Yesew Astamami) - ደረጀ ፡ ከበደ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ደረጀ ፡ ከበደ
(Dereje Kebede)

Dereje Kebede 9.jpg


(9)

የአድናቆት ፡ ቀን ፡ ለእግዚአብሔር
(Yeadnaqot Qen LeEgziabhier)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፪ (2010)
ቁጥር (Track):

(8)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የደረጀ ፡ ከበደ ፡ አልበሞች
(Albums by Dereje Kebede)

የሰው ፡ አስታማሚ ፡ ውሱን ፡ ነው ፡ ስልቹ
ይርዳሉ ፡ እጆቹ ፡ ይከብዳሉ ፡ ዓይኖቹ
የሰው ፡ አስታማሚ ፡ ጥቂት ፡ ነው ፡ ትዕግስቱ
እግዚአብሔር ፡ ግን ፡ ታማኝ ፡ ቅርብ ፡ ለጠሩቱ
እግዚአብሔር ፡ ግን ፡ ታማኝ

በራችሁ ፡ ተዘግቶ ፡ ተረሳን ፡ ያላችሁ
ውኃ ቀና ፡ አድርጐ ፡ ጠፍቶ ፡ የሚያጠጣችሁ
በሩቁም ፡ በቅርቡ ፡ በያላችሁበት
ቁስላችሁ ፡ ይጠገን ፡ በጌታ ፡ ምህረት
ቁስላችሁ ፡ ይጠገን

ማነው ፡ የሚገደው ፡ ለእነኛ ፡ አቅም ፡ ላጡት
ፀሐይ ፡ ለማይሞቁ ፡ ደጅ ፡ ለማይውጡ
ከዓይናችን ፡ ከጠፉ ፡ ፈጥነው ፡ ይረሳሉ
ኩርሲያቸው ፡ ተወስዶ ፡ እያሉ ፡ እንደሌሉ

አዝ፦ ከአጥር ፡ ውዲህ ፡ ተከማችተን
ጭፍራ ፡ ዝላዩን ፡ ትተን
እስቲ ፡ እንውጣ ፡ ከአዳራሹ
ፍቅር ፡ ድጋፍ ፡ ወደሚሹ

ፌጦው ፡ ድንገተኛው ፡ ሁሉ ፡ ተሞክሮ
ሃኪሙም ፡ ሳይታክት ፡ በጥበብ ፡ በአይምሮ
በሩቅ ፡ በጐረቤት ፡ ተመክሮ ፡ ተዘክሮ
እልፍ ፡ አልተገኘም ፡ ተጥሮ ፡ ተግሮ

በህክምና ፡ ሂደት ፡ መድኃኒት ፡ ቅመማ
በሳይንስ ፡ ጥናት ፡ በሊቆች ፡ ግምገማ
የዕድሜያችሁ ፡ መጽሃፍ ፡ ተከድኗል ፡ ያሉአችሁ
ወደ ፡ ፈዋሽ፡ አምላክ ፡ ይመልከት ፡ ዓይናችሁ
ወደ ፡ ፈዋሽ፡ አምላክ

ማነው ፡ የሚገደው ፡ ለእነኛ ፡ አቅም ፡ ላጡት
ፀሐይ ፡ ለማይሞቁ ፡ ደጅ ፡ ለማይውጡ
ከዓይናችን ፡ ከጠፉ ፡ ፈጥነው ፡ ይረሳሉ
ኩርሲያቸው ፡ ተወስዶ ፡ እያሉ ፡ እንደሌሉ

አዝ፦ ከአጥር ፡ ውዲህ ፡ ተከማችተን
ጭፍራ ፡ ዝላዩን ፡ ትተን
እስቲ ፡ እንውጣ ፡ ከአዳራሹ
ፍቅር ፡ ድጋፍ ፡ ወደሚሹ

ህመማችሁ ፡ ጸንቶ ፡ ቀና ፡ የማትሉት
ፋታ ፡ የማይሰጣችሁ ፡ ውጋት ፡ ቀርጥማቱ
ውሉ ፡ የጠፋችሁ ፡ የቀን ፡ የሌሊቱ
ጌታ ፡ ይዳብሳችሁ ፡ ባላችሁበቱ

በበሽታ ፡ አቅምህ ፡ የለ
ሥጋ ፡ አጥንትህ ፡ የሰለለ
በፍራቻ ፡ ባሕር ፡ ስምጠት
ሰውም ፡ ከቦህ ፡ ብቸኝነት
ከሃኪሙ ፡ ተስፋ ፡ አጥተሃል
ጤና ፡ አዳሙም ፡ ሰልችቶሃል
እዛው ፡ ባልጋው ፡ ባለህበት
ፈዋሹ ፡ አምላክ ፡ ይንካህ ፡ ድንገት