ይነጫነጭ ፡ ጠላት (Yenechanech Telat) - ደረጀ ፡ ከበደ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ደረጀ ፡ ከበደ
(Dereje Kebede)

Dereje Kebede 9.jpg


(9)

የአድናቆት ፡ ቀን ፡ ለእግዚአብሔር
(Yeadnaqot Qen LeEgziabhier)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፪ (2010)
ቁጥር (Track):

(5)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የደረጀ ፡ ከበደ ፡ አልበሞች
(Albums by Dereje Kebede)

ፀሐይ ፡ ፈነጠቀች ፡ ደረሰ ፡ ጠዋቱ
ድምጼም ፡ ያስተጋባ ፡ የገደል ፡ ማሚቱ
እግዚአብሔርን ፡ ልጥራ ፡ በውዳሴ ፡ አሃዱ
ይነጫነጭ ፡ ጠላት ፡ ያው ፡ እንደልማዱ (፫x)

ተመቻችቶ ፡ ነበር ፡ እርስቱን ፡ አስፍቶ
ዝምታዬ ፡ ጣፍጦት ፡ ሲቧርቅ ፡ ሰንብቶ
ስለቴ ፡ ደርሶልኝ ፡ ለእግዚአብሔር ፡ ብዘምር
ሽብር ፡ ተፈጠረ ፡ በዲያብሎስ ፡ ቅጥር

በማለዳ ፡ ዜማ ፡ እግዚአብሔር ፡ ከበረ
ክፋት ፡ ሸራቢው ፡ ግን ፡ ዲያብሎስ ፡ አፈረ
እርሱ ፡ እንዳሻው ፡ ይሁን ፡ የሲኦሉ ፡ ሲሳይ
እኔ ፡ ግን ፡ ልዘምር ፡ ላለው ፡ ዙፋኑ ፡ ላይ

በክረምት ፡ በበጋ ፡ በህመም ፡ በጤና
በክብር ፡ በውርደት ፡ በድል ፡ እንደገና
በማግኘት ፡ በማጣት ፡ በትርፍ ፡ በኪሳራ
ስንቱን ፡ አቋርጠናል ፡ ከእግዚአብሔር ፡ ጋራ

ፀሐይ ፡ ፈነጠቀች ፡ ደረሰ ፡ ጠዋቱ
ድምጼም ፡ ያስተጋባ ፡ የገደል ፡ ማሚቱ
እግዚአብሔርን ፡ ልጥራ ፡ በውዳሴ ፡ አሃዱ
ይነጫነጭ ፡ ጠላት ፡ ያው ፡ እንደልማዱ (፫x)

ዙሬያየን ፡ የማየው ፡ እልልም ፡ ባያሰኝ
የክብሩን ፡ መስዋእት ፡ ልነፍግ ፡ እኔ ፡ ማን ፡ ነኝ
በዘመነ ፡ መልካም ፡ ወይ ፡ ዘመን ፡ ቁዛሜ
እወድሰዋለሁ ፡ በሰዎች ፡ ፊት ፡ ቆሜ

ጆሯችንን ፡ ሰርቆ ፡ ሹክ ፡ የሚለን ፡ ጠላት
ሰፍሮ ፡ ትከሻችን ፡ ሲጭንብን ፡ መዓት
ማርከሻው ፡ መዝሙር ፡ ነው ፡ ለእግዚአብሔር ፡ ምሥጋና
ጥንትም ፡ የኢየሱስ ፡ ሥም ፡ መች ፡ ይበገርና

በክረምት ፡ በበጋ ፡ በህመም ፡ በጤና
በክብር ፡ በውርደት ፡ በድል ፡ እንደገና
በማግኘት ፡ በማጣት ፡ በትርፍ ፡ በኪሳራ
ስንቱን ፡ አቋርጠናል ፡ ከእግዚአብሔር ፡ ጋራ

ፀሐይ ፡ ፈነጠቀች ፡ ደረሰ ፡ ጠዋቱ
ድምጼም ፡ ያስተጋባ ፡ የገደል ፡ ማሚቱ
እግዚአብሔርን ፡ ልጥራ ፡ በውዳሴ ፡ አሃዱ
ይነጫነጭ ፡ ጠላት ፡ ያው ፡ እንደልማዱ (፫x)

በቃላቶች ፡ ውበት ፡ ጤም ፡ ባለው ፡ ዜማ
ተነሱ ፡ እንወድስ ፡ ድምጻችን ፡ ይሰማ ፡
የልባችን ፡ ክብደት ፡ አስጨናቂው ፡ ሁሉ
እንደ ፡ እያሪኮ ፡ ግንብ ፡ ይናዳል ፡ ከውሉ