ተለይተው ፡ ከእኛ (Teleyetew Kegna) - ደረጀ ፡ ከበደ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ደረጀ ፡ ከበደ
(Dereje Kebede)

Dereje Kebede 9.jpg


(9)

የአድናቆት ፡ ቀን ፡ ለእግዚአብሔር
(Yeadnaqot Qen LeEgziabhier)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፪ (2010)
ቁጥር (Track):

(4)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የደረጀ ፡ ከበደ ፡ አልበሞች
(Albums by Dereje Kebede)

አዝ፦ ከሰፈር ፡ ሰፈር
ውጭ ፡ ጉዋሮው ፡ ሳየቀር
ከበራፍ ፡ በራፍ
ከቶ ፡ አንድም ፡ ቤት ፡ ሳታልፍ
አጽናኝ ፡ መንፈስ ፡ ሆይ ፡ ፈጥነህ ፡ ድረስ ፡ ለእኛ
የምንወዳቸው ፡ ተለይተው ፡ ከእኛ
እስከመቼ ፡ ድረስ ፡ ሆነን ፡ ሃዘንተኛ

ሰውማ ፡ ዛሬም ፡ ላይ ፡ ታች ፡ ይላል
አደባባዩስ ፡ መቼ ፡ ይጐላል
ጨዋ ፡ ህዝብ ፡ ፈገግታ ፡ ያሳያል
ልቡ ፡ ግን ፡ በሃዘን ፡ ይጋያል

ወንድ ፡ ሴት ፡ ልጆቹን ፡ ያጣ ፡ ሰው
እህቱን ፡ ወንድሙን ፡ ያጣ ፡ ሰው
ወላጆቹን ፡ በሞት ፡ ያጣ ፡ ሰው
ያጽናኝ ፡ ያለህ ፡ ይላል ፡ ሆዱን ፡ እየባሰው

አዝ፦ ከሰፈር ፡ ሰፈር
ውጭ ፡ ጉዋሮው ፡ ሳየቀር
ከበራፍ ፡ በራፍ
ከቶ ፡ አንድም ፡ ቤት ፡ ሳታልፍ
አጽናኝ ፡ መንፈስ ፡ ሆይ ፡ ፈጥነህ ፡ ድረስ ፡ ለእኛ
የምንወዳቸው ፡ ተለይተው ፡ ከኛ
እስከመቼ ፡ ድረስ ፡ ሆነን ፡ ሃዘንተኛ

ባልንጀር ፡ አብሮ ፡ አደጉን ፡ ያጣ
የሥራ ፡ ባልደራባዉን ፡ ያጣ
ጐረቤት ፡ ጠያቂውን ፡ ያጣ
የሚያጽናናው ፡ ዛሬ ፡ ከየት ፡ ይምጣ

ሞት ፡ ያልበዘበዘው ፡ ማን ፡ አለ
ቤት ፡ ጓዳው ፡ ያልተመሰቃቀለ
ተርታውን ፡ ከደጃፍ ፡ እደጃፍ
ነጣቂው ፡ ነጠቀ ፡ ከቶ ፡ አንድም ፡ ሳያልፍ

አዝ፦ ከሰፈር ፡ ሰፈር
ውጭ ፡ ጉዋሮው ፡ ሳየቀር
ከበራፍ ፡ በራፍ
ከቶ ፡ አንድም ፡ ቤት ፡ ሳታልፍ
አጽናኝ ፡ መንፈስ ፡ ሆይ ፡ ፈጥነህ ፡ ድረስ ፡ ለእኛ
የምንወዳቸው ፡ ተለይተው ፡ ከኛ
እስከመቼ ፡ ድረስ ፡ ሆነን ፡ ሃዘንተኛ

ህጻናት ፡ ተጣለ ፡ ባዶ ፡ ቤት
እናት ፡ አባት ፡ አልቀው ፡ በቅጽበት
ሽማግሌዎች ፡ ጡዋሪም ፡ የላቸው
ተቀጭተው ፡ ተስፋ ፡ ልጆቻቸው

የፍራቻ ፡ ጥላ ፡ የሥጋት
ሰንብቶአል ፡ ምድሪቱን ፡ ከዋጣት
ጠዋት ፡ ያዩት ፡ በሕይወት ፡ ለማታ
በነበር ፡ ይወሳል ፡ በቅጽበት ፡ በአንዳፍታ

አዝ፦ ከሰፈር ፡ ሰፈር
ውጭ ፡ ጉዋሮው ፡ ሳየቀር
ከበራፍ ፡ በራፍ
ከቶ ፡ አንድም ፡ ቤት ፡ ሳታልፍ
አጽናኝ ፡ መንፈስ ፡ ሆይ ፡ ፈጥነህ ፡ ድረስ ፡ ለእኛ
የምንወዳቸው ፡ ተለይተው ፡ ከኛ
እስከመቼ ፡ ድረስ ፡ ሆነን ፡ ሃዘንተኛ

ምናልባት ፡ ብትራራ ፡ ጌታችን
የእንጨት ፡ ርብራብ ፡ ሆኗአል ፡ ቤታችን
አሳር ፡ ነው ፡ ዞሮም ፡ መግባቱ
አባዜው ፡ ክፍ ፡ ሆኖ ፡ የቤቱ

ያልፋል ፡ ይህ ፡ የከፍ ፡ ቀን
እግዚአብሔር ፡ በምረት ፡ ሲያውቀን
ስብራት ፡ ይጠገንና
የዓይናችን ፡ እንባ ፡ ፍፁም ፡ ይደርቅና
የትናንት ፡ ወሬ ፡ ይሆንና
ይሞላል ፡ ሰው ፡ በምሥጋና