From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
የቆምኩበት ፡ ስፍራ ፡ ይህ ፡ ግዑዙ ፡ መሬት ፡ ግዑዙ ፡ መሬት
የሰላም ፡ ነው ፡ የደም ፡ ጠብ ፡ የበቀለበት ፡ ጠብ ፡ የበቀለበት
የእርምጃዬ ፡ ማብቂያ ፡ የእግሮቸን ፡ አቅጣጫ ፡ የእግሮቸን ፡ አቅጣጫ
መርምር ፡ ሩጫዬን ፡ የሕይወቴን ፡ ምርጫ ፡ የሕይወቴን ፡ ምርጫ ፡
የሕይወቴን ፡ ምርጫ ፡ የሕይወቴን ፡ ምርጫ
ልቤን ፡ ብትከፍተው ፡ ጫካኝ ፡ ነው ፡ ወይ ፡ ገራም ፡ ጫካኝ ፡ ነው ፡ ወይ ፡ ገራም
የእጆቸ ፡ መዘርጋት ፡ ለሰይፍ ፡ ነው ፡ ለሰላም ፡ ለሰይፍ ፡ ነው ፡ ለሰላም
ሌሊት ፡ በምንጣፌ ፡ በጭርታው ፡ ሰዓት ፡ በጭርታው ፡ ሰዓት
የማውጠነጥነው ፡ የአዕምሮዬ ፡ ሙላት ፡ የአዕምሮዬ ፡ ሙላት
የአዕምሮዬ ፡ ሙላት የአዕምሮዬ ፡ ሙላት
ከአንተ ፡ (፫ጊዜ) ምን ፡ የደበቃል
ፍጥረት ፡ እርቃኑን ፡ ነው ፡ ግልጥልጥ ፡ ብሏል
ድልድል ፡ ቢሆን ፡ወይ ገደላማ
በራ ፡ ቢሆን፡ ወይ ፡ ደመናማ
እዚህ ፡ በቅርብ ፡ ወይ ፡ እዚያ ፡ በሩቅ
ደረቅ ፡ መሬት ቢሆን፡ ወይ ፡ ውኃ ጥልቅ
በምድር ፡ በታች ፡ በአየር ፡ በላይ
የሚያልፍህ ፡ የለም ፡ ዓይንህ ፡ ሳያይ
ከአንተ ፡ (፫ጊዜ) ምን ፡ የደበቃል
ዓይኖቼ ፡ ተከፍተው ፡ ወዴት ፡ አማተሩ ፡ ወዴት ፡ አማተሩ
የምላሴ ፡ ቅምሻ ፡ ጣፋጭ ፡ ነው ፡ መራሩ ፡ ጣፋጭ ፡ ነው ፡ መራሩ
ቃሌ ፡ የአንደበቴ ፡ የሚወረወረው ፡ የሚወረወረው
ለጐረቤት ፡ ጆሮ ፡ በራድ ፡ ወይ ፡ እሳት ፡ ነው ፡ በራድ ፡ ወይ ፡ እሳት ፡ ነው
በራድ ፡ ወይ ፡ እሳት ፡ ነው ፡ በራድ ፡ ወይ ፡ እሳት ፡ ነው
የፊቴ ፡ ገታ ፡ ውጫዊ ፡ ምስሌ ፡ ውጫዊ ፡ ምስሌ
ላየኝ ፡ በሩቅ ፡ መሳይ ፡ ሁሉን ፡ መደለሌ ፡ ሁሉን ፡ መደለሌ
ከብላቴንነት ፡ ከቶ ፡ መች ፡ ጠቀመኝ ፡ ከቶ ፡ መች ፡ ጠቀመኝ
ውስጤን ፡ የምታይ ፡ ሆይ ፡ ዛሬ ፡ ግን ፡ መርምረኝ ፡ ዛሬ ፡ ግን ፡ መርምረኝ
ዛሬ ፡ ግን ፡ መርምረኝ ፡ ዛሬ ፡ ግን ፡ መርምረኝ
ከአንተ ፡ (፫ጊዜ) ምን ፡ የደበቃል
ፍጥረት ፡ እርቃኑን ፡ ነው ፡ ግልጥልጥ ፡ ብሏል
ድልድል ፡ ቢሆን ፡ ገደላማ
ብራ ፡ ቡሆን ፡ ወይ ፡ ደመናማ
እዚህ ፡ በቅርብ ፡ ወይ ፡ እዚያ ፡ በሩቅ
ደረቅ ፡ መሬት ፡ ወይ ፡ ውኃ ጥልቅ
በምድር ፡ በታች ፡ በአየር ፡ በላይ
የሚያልፍ ፡ የለም ፡ ዓይንህ ፡ ሳያይ
ከአንተ ፡ (፫ጊዜ) ምን ፡ የደበቃል
|