ምህረት ፡ አልወረደም (Meheret Alweredem) - ደረጀ ፡ ከበደ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ደረጀ ፡ ከበደ
(Dereje Kebede)

Dereje Kebede 9.jpg


(9)

የአድናቆት ፡ ቀን ፡ ለእግዚአብሔር
(Yeadnaqot Qen LeEgziabhier)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፪ (2010)
ቁጥር (Track):

(9)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የደረጀ ፡ ከበደ ፡ አልበሞች
(Albums by Dereje Kebede)

እየመሽ ፡ ነጋ ፡ እየነጋም ፡ መሽ
ዛሬም ፡ ጉስቁልና ፡ ከምድሪቱ ፡ እልሸሸ
ሁካቴ ፡ የፀናበት ፡ የአልጋ ፡ ቁራኛ ፡ ሰው
ታሞ ፡ ማያገግም ፡ ማቁን ፡ አለበሰው
ቀባሪ ፡ ደከመው ፡ ግራ ፡ ቅኝ ፡ እሬሳ
ሃዘን ፡ ተቀማጩም ፡ ዛሬም ፡ አልተነሳ
ጥቁር ፡ የለበሰ ፡ የተላጨ ፡ ፀጉሩ
ወዳጁን ፡ ያጣ ፡ ሰው ፡ ፈሷል ፡ በመንደሩ ፡ አሂሂ ፡ ፈሷል ፡ በመንደሩ

ዛሬም ፡ ገና ፡ ነው
ገና ፡ ነው ፡ ምህረቱ ፡ አልወረደም
የሃገሬ ፡ ንዳድ ፡ ዛሬም ፡ አልበረደም ፡ አዎ ፡
ገና ፡ ነው ፡ ቁጣው ፡ መቸ ፡ ሰከነ
በሽታና ፡ ርሃብ ፡ ባገሬ ፡ በወንዜ፡ ገነነ

ከማዶ ፡ ይሰማል ፡ እሪታ ፡ ከሩቅ
የሞት ፡ ልጆች ፡ ለቅሶ ፡ ዋይታ ፡ የሚሰቅቅ
አፅናኝ ፡ ሆይ ፡ ውረድ ፡ ወደ ፡ ምድር
ምሕረትህ ፡ ይጐብኘን ፡ ይውደቅ ፡ የሞት ፡ በትር
አፅናኝ ፡ ሆይ

ማረን ፡ ጌታችን ፡ ፈጽመህ ፡ አትቅጣን
ጠበልክን ፡ እርጨን ፡ ጠምቶናል ፡ አጠጣን
ታማሚው ፡ ይፈወስ ፡ የራበው ፡ ሰው ፡ ይጥገብ
የፍርድ ፡ አዋጅ ፡ በቅቶ ፡ ምህረቱ ፡ ይነበብ

ከትናንት ፡ ዛሬ ፡ ይሻል ፡ ይሆን ፡ ብለን
የበጐ ፡ ቀን ፡ ያለህ ፡ አልመጣም ፡ ጠብቀን
የነገዋ ፡ ፀሐይ ፡ ሙቀት ፡ ይዛ ፡ ትምጣ
የሃገር ፡ ልጅ ፡ በርዶታል ፡ ድሪቶም ፡ ስላጣ
በረሃብ ፡ ጉስቁልና ፡ በጥማት ፡ ተቃጥሎ
በብርድ ፡ ተጠብሶ ፡ በፀሐይ ፡ ከሳስሎ
ኑሮ ፡ እንደሬት ፡ መሮት ፡ ለሞቱ ፡ የሚጐመጅ
በጐዳናው ፡ ከፈፍ ፡ ተዘርግቷል ፡ እድጅ ፡ አሂሂ ፡ ተዘርግቷል ፡ እደጅ

ዛሬም ፡ ገና ፡ ነው
ገና ፡ ነው ፡ ምህረቱ ፡ አልወረደም
የሃገሬ ፡ ንዳድ ፡ ዛሬም ፡ አልበረደም ፡ አዎ ፡
ገና ፡ ነው ፡ ቁጣው ፡ መቸ ፡ ሰከነ
በሽታና ፡ ርሃብ ፡ ባገሬ ፡ በወንዜ፡ ገነነ

ከማዶ ፡ ይሰማል ፡ እሪታ ፡ ከሩቅ
የሞት ፡ ልጆች ፡ ለቅሶ ፡ ዋይታ ፡ የሚሰቅቅ
አፅናኝ ፡ ሆይ ፡ ውረድ ፡ ወደ ፡ ምድር
ምሕረትህ ፡ ይጐብኘን ፡ ይውደቅ ፡ የሞት ፡ በትር
አፅናኝ ፡ ሆይ

ማረን ፡ ጌታችን ፡ ፈጽመህ ፡ አትቅጣን
ጠበልክን ፡ እርጨን ፡ ጠምቶናል ፡ አጠጣን
ታማሚው ፡ ይፈወስ ፡ የራበው ፡ ሰው ፡ ይጥገብ
የፍርድ ፡ አዋጅ ፡ በቅቶ ፡ ምህረቱ ፡ ይነበብ

ክራራይሶ (፪x) ፡ እግዚኦ ፡ ማሃረነ ፡ ክርስቶስ (፪x)