እግዚአብሔር ፡ የታል ፡ ለምን ፡ ትለኛለህ (Egziabhier Yetal Lemen Telegnaleh) - ደረጀ ፡ ከበደ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ደረጀ ፡ ከበደ
(Dereje Kebede)

Dereje Kebede 9.jpg


(9)

የአድናቆት ፡ ቀን ፡ ለእግዚአብሔር
(Yeadnaqot Qen LeEgziabhier)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፪ (2010)
ቁጥር (Track):

፲ ፩ (11)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የደረጀ ፡ ከበደ ፡ አልበሞች
(Albums by Dereje Kebede)

እግዚአብሔር ፡ የታል ፡ ለምን ፡ ትለኛለህ
ፍጥረታት ፡ በዙሪያህ ፡ ከበውህ ፡ እያየህ
ዓይን ፡ አጥርቶ ፡ ቢያይ ፡ ጆሮችህ ፡ ቢያቀኑ
የእርሱን ፡ ህልውና ፡ ታይ ፡ ነበር ፡ በውኑ

ውጣ ፡ ወደ ፡ ሜዳው ፡ ሂድ ፡ ወደ ፡ ሃይቁ
የፍጥረትን ፡ ሰሪ ፡ ቢያሻህ ፡ መጠየቁ
አቀበቱን ፡ ውጣ ፡ ቁልቁለቱን ፡ ውረድ
ሜዳ ፡ ለጥ ፡ ያለውን ፡ ወይ ፡ ረዥሙን ፡ መንገድ
በደረስክበቱ ፡ የሰማህ ፡ ያየኸው
ሰሪና ፡ ተካዩ ፡ ሕያው ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው

እያት ፡ ቢራቢሮ ፡ ተፈጥሮ ፡ ያስጌጣት
ክንፎቹዋ ፡ ርግብግብ ፡ ውበት ፡ የተሰጣት
ተመልከት ፡ ወፊቱን ፡ ጐጆ ፡ ስትራ
መሰረቱን ፡ ጥላ ፡ ለፍታ ፡ ጥራ ፡ ግራ
የትም ፡ ዞራ ፡ ዞራ ፡ በአየር ፡ በደመና
ተመልሳ ፡ ቤቷ ፡ ሳትስት ፡ ጐዳና

አዝ፦ እግዚአብሔርን ፡ በእጅህ ፡ ቢያሻህ ፡ ለመዳሰስ
የልብህን ፡ ጥያቄ ፡ ምናልባት ፡ ቢመለስ
ተመልከት ፡ ፍጥረትን ፡ የሰራውን ፡ በእጁ
ወጥተህ ፡ ወደ ፡ ደጁ

እግዚአብሔር ፡ የታል ፡ ለምን ፡ ትለኛለህ
ፍጥረታት ፡ በዙሪያህ ፡ ከበውህ ፡ እያየህ
ዓይን ፡ አጥርቶ ፡ ቢያይ ፡ ጆሮችህ ፡ ቢያቀኑ
የእርሱን ፡ ህልውና ፡ ታይ ፡ ነበር ፡ በውኑ

ነፋሱም ፡ ያፏጫል ፡ ዛፉም ፡ ይራወጣል
ጂረቱም ፡ ይፈሳል ፡ ምንጩም ፡ ያው ፡ ይፈልቃል
ቀን ፡ ለፀሐይ ፡ መውጫ ፡ ማታው ፡ ለጨረቃ
ጨለማና ፡ ብርሃን ፡ በተራ ፡ ጥበቃ
ወቅት ፡ ሲፈራረቅ ፡ ዛሬም ፡ እንደጥንቱ
እግዚአብሔር ፡ ያውልህ ፡ እየው ፡ በፍጥረቱ

ከፀሐይ ፡ ባሻገር ፡ ብዙ ፡ ዘመን ፡ ርቀት
እልፍ ፡ አእላፍ ፡ ክዋክብት ፡ ያሸበረቀበት
ዓሣ ፡ ነባሪውም ፡ በውቂያኖስ ፡ ጥልቀት
አናብስቱ ፡ በዱር ፡ ሲያገሱ ፡ በርቀት
ገብረ ፡ ጉንዳን ፡ ሰልፉ ፡ ሁከት ፡ የሌለበት
ውብ ፡ ፍጥረት ፡ ዙሪያህን ፡ አልመጣ ፡ እንደድንገት

አዝ፦ እግዚአብሔርን ፡ በእጅህ ፡ ቢያሻህ ፡ ለመዳሰስ
የልብህን ፡ ጥያቄ ፡ ምናልባት ፡ ቢመለስ
ተመልከት ፡ ፍጥረትን ፡ የሰራውን ፡ በእጁ
ወጥተህ ፡ ወደ ፡ ደጁ