ዘመኑ ፡ አስፈሪ ፡ ቢሆንም (Zemenu Asferi Bihonem) - ደረጀ ፡ ከበደ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ደረጀ ፡ ከበደ
(Dereje Kebede)

Lyrics.jpg


(4)

መንግሥተ ፡ ሰማይ
(Mengeste Semay)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፸ ፪ (1980)
ቁጥር (Track):

፲ ፭ (15)

ርዝመት (Len.): 4:14
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የደረጀ ፡ ከበደ ፡ አልበሞች
(Albums by Dereje Kebede)

አዝ፦ ዘመኑ ፡ አስፈሪ ፡ ቢሆንም
የጌታ ፡ ፀጋ ፡ አላነሰንም
ዲያቢሎስ ፡ ቢራቀቅ ፡ ቢመጥቅ ፡
አይተኛም ፡ እኛን ፡ የሚጠብቅ (፪x)

እርግጥ ፡ ነው ፡ ጠላታችን ፡ እጅግ ፡ ተራቋል
መጠላለፊያውን ፡ ሰውሮ ፡ አስቀምጧል
ምድርን ፡ በእጁ ፡ አድርጐ ፡ ይጫወትባታል
ለእኛ ፡ ግን ፡ እግዚአብሔር ፡ እንዳለን ፡ ተረድቷል

አዝ፦ ዘመኑ ፡ አስፈሪ ፡ ቢሆንም
የጌታ ፡ ፀጋ ፡ አላነሰንም
ዲያቢሎስ ፡ ቢራቀቅ ፡ ቢመጥቅ ፡
አይተኛም ፡ እኛን ፡ የሚጠብቅ (፪x)

ሃያ ፡ እጥፍ ፡ ቢያነድም ፡ እሳቱን ፡ ሊያስበላን
የሚያጠውፋው ፡ ውኃ ፡ ኢየሱስ ፡ አለልን
ባህሩን ፡ ቢያሰፋ ፡ ሊያሰምጠን ፡ ወደስር
መርከብ ፡ ሆኖ ፡ ማዶ ፡ አለን ፡ የሚያሻግር

አዝ፦ ዘመኑ ፡ አስፈሪ ፡ ቢሆንም
የጌታ ፡ ፀጋ ፡ አላነሰንም
ዲያቢሎስ ፡ ቢራቀቅ ፡ ቢመጥቅ ፡
አይተኛም ፡ እኛን ፡ የሚጠብቅ (፪x)

ምድርን ፡ ለቆ ፡ ሰይጣን ፡ በአየር ፡ እየሮጠ
ሊያዳክም ፡ የአማኝን ፡ በሩን ፡ ቀጠቀጠ
የክርስቲያን ፡ መዝጊያው ፡ አይበገር ፡ ኖሮ
መና ፡ ቀረ ፡ ጠላት ፡ ያለ ፡ ኃይሉን ፡ ጥሎ

አዝ፦ ዘመኑ ፡ አስፈሪ ፡ ቢሆንም
የጌታ ፡ ፀጋ ፡ አላነሰንም
ዲያቢሎስ ፡ ቢራቀቅ ፡ ቢመጥቅ ፡
አይተኛም ፡ እኛን ፡ የሚጠብቅ (፪x)

ወጥመዱ ፡ በርትቶ ፡ ሊያጠምደን ፡ ቢጣጣር
ሕያው ፡ አምላካችን ፡ ይዋጋል ፡ ከእኛ ፡ ጋር
የጽዮን ፡ አርበኛ ፡ ቆራጥ ፡ የታጠቀ
አንዴም ፡ አልተረታ ፡ አንዴም፡ አልወደቀ

አዝ፦ ዘመኑ ፡ አስፈሪ ፡ ቢሆንም
የጌታ ፡ ፀጋ ፡ አላነሰንም
ዲያቢሎስ ፡ ቢራቀቅ ፡ ቢመጥቅ ፡
አይተኛም ፡ እኛን ፡ የሚጠብቅ (፪x)