የንጋቱ ፡ ኮከብ ፡ አበራ (Yenegatu Kokeb Abera) - ደረጀ ፡ ከበደ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ደረጀ ፡ ከበደ
(Dereje Kebede)

Lyrics.jpg


(4)

መንግሥተ ፡ ሰማይ
(Mengeste Semay)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፸ ፪ (1980)
ቁጥር (Track):

(5)

ርዝመት (Len.): 4:28
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የደረጀ ፡ ከበደ ፡ አልበሞች
(Albums by Dereje Kebede)

አዝ፦ የንጋቱ ፡ ኮከብ ፡ አበራ
ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ በሁሉም ፡ ስፍራ
ማን ፡ ያግደው ፡ ማን ፡ ይታገለው
ይቆራርጣል ፡ ቃሉ ፡ ሰይፍ ፡ ነው
ማን ፡ ያግደው ፡ ማን ፡ ይታገለው (፪x)

በዓለም ፡ ነግሰው ፡ ኃያል ፡ ነን ፡ ያሉት
ትንሳኤህን ፡ ሽረው ፡ ሞትህን ፡ ሊያስወሩ
ብዙ ፡ ለፉ ፡ ላይሆንላቸው
ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ አሸነፋቸው (፪x)

አዝ፦ የንጋቱ ፡ ኮከብ ፡ አበራ
ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ በሁሉም ፡ ስፍራ
ማን ፡ ያግደው ፡ ማን ፡ ይታገለው
ይቆራርጣል ፡ ቃሉ ፡ ሰይፍ ፡ ነው
ማን ፡ ያግደው ፡ ማን ፡ ይታገለው (፪x)

በእሳት ፡ በውኃ ፡ የእግዚአብሔርን ፡ ቃል
ከምር ፡ ሊያጠፋ ፡ እጅግ ፡ አልሟል
የምስራቹ ፡ አንዳይሰማ
ጠላት ፡ ጣረ ፡ በጭፍራው ፡ አድማ (፪x)

አዝ፦ የንጋቱ ፡ ኮከብ ፡ አበራ
ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ በሁሉም ፡ ስፍራ
ማን ፡ ያግደው ፡ ማን ፡ ይታገለው
ይቆራርጣል ፡ ቃሉ ፡ ሰይፍ ፡ ነው
ማን ፡ ያግደው ፡ ማን ፡ ይታገለው (፪x)

አዝ፦ የንጋቱ ፡ ኮከብ ፡ አበራ
ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ በሁሉም ፡ ስፍራ
ማን ፡ ያግደው ፡ ማን ፡ ይታገለው
ይቆራርጣል ፡ ቃሉ ፡ ሰይፍ ፡ ነው
ማን ፡ ያግደው ፡ ማን ፡ ይታገለው (፪x)

ነገሥታቶች ፡ ሰይፍ ፡ መዘዙ
ገናና ፡ ሆነው ፡ ምድርን ፡ ሊገዙ
ኢየሱስ ፡ ግን ፡ ከአሪያም ፡ ተቀምጦ
ሁሉን ፡ ገዛ ፡ ታሪክ ፡ ለውጦ (፪x)

አዝ፦ የንጋቱ ፡ ኮከብ ፡ አበራ
ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ በሁሉም ፡ ስፍራ
ማን ፡ ያግደው ፡ ማን ፡ ይታገለው
ይቆራርጣል ፡ ቃሉ ፡ ሰይፍ ፡ ነው
ማን ፡ ያግደው ፡ ማን ፡ ይታገለው (፫x)