From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
አዝ፦ ትህትና ፡ ሊያስተምረኝ ፡ ወዶ
እግር ፡ አጠበ ፡ ባርያውን ፡ ወርዶ
እራሱን ፡ አዋርዶ (፪x)
ደቀ ፡ መዛሙርቱ ፡ አግራቸው ፡ ቆሸሸ
አደፈ ፡ ጐደፈ ፡ ፍፁም ፡ ተበላሸ
ሁሉን ፡ የፈጠረ ፡ ሰውን ፡ የወደደ
ጭቃውን ፡ ሊያስወግድ ፡ ወደታች ፡ ወረደ
አዝ፦ ትህትና ፡ ሊያስተምረኝ ፡ ወዶ
እግር ፡ አጠበ ፡ ባርያውን ፡ ወርዶ
እራሱን ፡ አዋርዶ (፪x)
እርሱ ፡ ያላጠበው ፡ ከእርሱ ፡ ጋር ፡ አይኖርም
አይቆርስም ፡ ከአምላክ ፡ ጋራ ፡ አንድነት ፡ የለውም
ጴጥሮስ ፡ ይህን ፡ አይቶ ፡ ሰውነቴን ፡ ደግሞ
እጠበኝ ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ አለውም ፡ ተማጽኖ
አዝ፦ ትህትና ፡ ሊያስተምረኝ ፡ ወዶ
እግር ፡ አጠበ ፡ ባርያውን ፡ ወርዶ
እራሱን ፡ አዋርዶ (፪x)
በሚደነቅ ፡ ብርሃን ፡ የሚኖር ፡ ፈጣሪ
አልፋና ፡ ኦሜጋ ፡ የፍጥረታት ፡ ሰሪ
ማበሻ ፡ ጨርቅ ፡ ወስዶ ፡ እግር ፡ ሊያጥብ ፡ ወረደ
ዝቅ ፡ አደረገ ፡ እራሱን ፡ ለሰው ፡ አዋረደ
አዝ፦ ትህትና ፡ ሊያስተምረኝ ፡ ወዶ
እግር ፡ አጠበ ፡ ባርያውን ፡ ወርዶ
እራሱን ፡ አዋርዶ (፪x)
የሁሉ ፡ ማሰሪያ ፡ አላማ ፡ ያለው ፡ ነው
ጌታ ፡ ይህን ፡ አድርጓል ፡ እኔስ ፡ እንደምነው
የወንድሜን ፡ እግር ፡ እስካጥብ ፡ ዝልቅ ፡ ካልኩ
እውነትም ፡ ኢየሱስን ፡ በእርግጥ ፡ ተከተልኩ
አዝ፦ ትህትና ፡ ሊያስተምረኝ ፡ ወዶ
እግር ፡ አጠበ ፡ ባርያውን ፡ ወርዶ
እራሱን ፡ አዋርዶ (፪x)
ባሪያ ፡ ከሚያኖረው ፡ አይበልጥም ፡ አላቸው
መልዕክተኛም ፡ አይበጅ ፡ ይልቁን ፡ ከላከው
እንግዲህ ፡ ጌታችሁ ፡ እኔ ፡ ይህን ፡ ስፈጽም
አድርጉት ፡ ለሁሉም ፡ ዛሬ ፡ ሁኑ ፡ እናንተም
አዝ፦ ትህትና ፡ ሊያስተምረኝ ፡ ወዶ
እግር ፡ አጠበ ፡ ባርያውን ፡ ወርዶ
እራሱን ፡ አዋርዶ (፪x)
|