ሰላም ፡ አለኝ (Selam Alegn) - ደረጀ ፡ ከበደ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ደረጀ ፡ ከበደ
(Dereje Kebede)

Lyrics.jpg


(4)

መንግሥተ ፡ ሰማይ
(Mengeste Semay)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፸ ፪ (1980)
ቁጥር (Track):

(10)

ርዝመት (Len.): 6:19
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የደረጀ ፡ ከበደ ፡ አልበሞች
(Albums by Dereje Kebede)

ቅብዝብዝነትን ፡ አጣሁት ፡ ከላዬ
መንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ ገዛው ፡ ዘልቆ ፡ ልቦናዬን
ኃይልን ፡ ከአርያም ፡ መልበሴን ፡ የማውቀው
የማያልፍ ፡ ሰላም ፡ ስላልተለየኝ ፡ ነው

አዝ፦ ሰላም ፡ አለኝ ፡ እንደወንዝ ፡ እንደወንዝ ፡ የሚፈስ
አዕምሮዬን ፡ የሚያረሰርስ
ደስታ ፡ አለኝ ፡ ከውስጤ ፡ ከውስጤ ፡ ማይጠፋ
ኢየሱስ ፡ ክብሩ ፡ ይስፋ ፡ ኡ.... (፪x)

ማነው ፡ የሚነጥቀኝ ፡ ይህንን ፡ ጸጥታ
የማይለየኝ ፡ ከውስጤ ፡ ለአንድ ፡ አፍታ
ከሰማይ ፡ ተገኝቶ ፡ ሰማያዊ ፡ የሆነ
ምድራዊማ ፡ ይሄኔ ፡ ትቶኝ ፡ በተነነ

አዝ፦ ሰላም ፡ አለኝ ፡ እንደወንዝ ፡ እንደወንዝ ፡ የሚፈስ
አዕምሮዬን ፡ የሚያረሰርስ
ደስታ ፡ አለኝ ፡ ከውስጤ ፡ ከውስጤ ፡ ማይጠፋ
ኢየሱስ ፡ ክብሩ ፡ ይስፋ ፡ ኡ.... (፪x)

እግዚአብሔር ፡ ይመስገን ፡ እንቅልፌን ፡ እተኛለሁ
አደራዬን ፡ ለእርሱ ፡ ለአምላኬ ፡ እጥላለሁ
የብረት ፡ መዝጊያዬ ፡ ኢየሱስ ፡ ሆኖልኛል
በእርሱ ፡ ተሸሽጌ ፡ ምንስ ፡ ይደፍረኛል

አዝ፦ ሰላም ፡ አለኝ ፡ እንደወንዝ ፡ እንደወንዝ ፡ የሚፈስ
አዕምሮዬን ፡ የሚያረሰርስ
ደስታ ፡ አለኝ ፡ ከውስጤ ፡ ከውስጤ ፡ ማይጠፋ
ኢየሱስ ፡ ክብሩ ፡ ይስፋ ፡ ኡ.... (፪x)

ጌታ ፡ መሰረቴ ፡ የማይነቃነቅ
ድጋፍ ፡ መጽንናኛዬ ፡ የሚያነሳኝ ፡ ስወድቅ
መናወጥ ፡ ከልቤ ፡ ጠፍቷል ፡ ላይመለስ
የሰላሜ ፡ ጌታ ፡ ይመስገን ፡ ኢየሱስ

አዝ፦ ሰላም ፡ አለኝ ፡ እንደወንዝ ፡ እንደወንዝ ፡ የሚፈስ
አዕምሮዬን ፡ የሚያረሰርስ
ደስታ ፡ አለኝ ፡ ከውስጤ ፡ ከውስጤ ፡ ማይጠፋ
ኢየሱስ ፡ ክብሩ ፡ ይስፋ ፡ ኡ.... (፫x)