መንገዴን ፡ በፊቱ ፡ አጸናለሁ (Megedien Befitu Atsenalehu) - ደረጀ ፡ ከበደ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ደረጀ ፡ ከበደ
(Dereje Kebede)

Lyrics.jpg


(4)

መንግሥተ ፡ ሰማይ
(Mengeste Semay)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፸ ፪ (1980)
ቁጥር (Track):

(3)

ርዝመት (Len.): 4:02
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የደረጀ ፡ ከበደ ፡ አልበሞች
(Albums by Dereje Kebede)

አዝ፦ ነገር ፡ ግን ፡ መንገዴን ፡ በፊቱ ፡ አጸናለሁ
ቢገድለኝም ፡ እንኳን ፡ እርሱን ፡ ጠብቃለሁ
እርሱን ፡ ጠብቃለሁ ፡ ጠብቃለሁ ፡ ጠብቃለሁ (፪x)

የሆነው ፡ ነገር ፡ ይምጣብኝ ፡ ሥጋዬን ፡ በጥርሴ ፡ እይዛለሁ
ቢገድለኝ ፡ እንኳን ፡ ታግሼ ፡ ሕይወቴን ፡ በእጁ ፡ አኖራለሁ
መድሃኒት ፡ ይሆንልኛል ፡ ነገሩ ፡ አይመረመርም
እጠብቀዋለሁ ፡ ጌታን ፡ በጥቂቱ ፡ ዝዬ ፡ አልወድቅም

አዝ፦ ነገር ፡ ግን ፡ መንገዴን ፡ በፊቱ ፡ አጸናለሁ
ቢገድለኝም ፡ እንኳን ፡ እርሱን ፡ ጠብቃለሁ
እርሱን ፡ ጠብቃለሁ ፡ ጠብቃለሁ ፡ ጠብቃለሁ (፪x)

በለስ ፡ እንኳን ፡ ባታፈራ ፡ የወይን ፡ ሃረግ ፡ ቢደርቅ
ዝም ፡ ብዬ ፡ የጌታን ፡ ቀን ፡ በትዕግሥት ፡ ልጠብቅ
የወራት ፡ ስራ ፡ ቢጐድል ፡ እርሾቼም ፡ ባያበሉኝ
እግዚአብሔር ፡ ኃይሌ ፡ ይሆናል ፡ ጥሩ ፡ ሰዓት ፡ ሲወጣልኝ

አዝ፦ ነገር ፡ ግን ፡ መንገዴን ፡ በፊቱ ፡ አጸናለሁ
ቢገድለኝም ፡ እንኳን ፡ እርሱን ፡ ጠብቃለሁ
እርሱን ፡ ጠብቃለሁ ፡ ጠብቃለሁ ፡ ጠብቃለሁ (፪x)

በውስጤ ፡ ስላደረው ፡ ተስፋ ፡ መንፈሱ ፡ አያሳፍረኝም
እንደ ፡ ኢዮብ ፡ ሳያጽናናኝ ፡ እግዚአብሔር ፡ ከቶ ፡ አይተወኝም
ከጋጣዬ ፡ የጠፉት ፡ ላሞች ፡ ነገ ፡ ይበራከታሉ
ያላገጡብኝ ፡ ጠላቶች ፡ የአምላኬን ፡ ስራ ፡ ያያሉ

አዝ፦ ነገር ፡ ግን ፡ መንገዴን ፡ በፊቱ ፡ አጸናለሁ
ቢገድለኝም ፡ እንኳን ፡ እርሱን ፡ ጠብቃለሁ
እርሱን ፡ ጠብቃለሁ ፡ ጠብቃለሁ ፡ ጠብቃለሁ (፪x)