መዳን ፡ ይሆንልናል (Medan Yehonelenal) - ደረጀ ፡ ከበደ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ደረጀ ፡ ከበደ
(Dereje Kebede)

Lyrics.jpg


(4)

መንግሥተ ፡ ሰማይ
(Mengeste Semay)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፸ ፪ (1980)
ቁጥር (Track):

(8)

ርዝመት (Len.): 3:15
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የደረጀ ፡ ከበደ ፡ አልበሞች
(Albums by Dereje Kebede)

አዝ፦ ለእኛስ ፡ ከሌላ ፡ ስፍራ ፡ መዳን ፡ ይሆንልናል (፪x)

በዓለም ፡ ምናምን ፡ ተስፋ ፡ አድርገን
ልባችን ፡ ረግቶ ፡ እፎይ ፡ ብለን
መኖር ፡ እንድንችል ፡ ብዙ ፡ ረባን
ሁሉ ፡ ግን ፡ ደቆ ፡ ኢየሱስ ፡ ቀረን

አዝ፦ ለእኛስ ፡ ከሌላ ፡ ስፍራ ፡ መዳን ፡ ይሆንልናል (፪x)

ወደ ፡ ተራራው ፡ በሮ ፡ ዓይናችን
ሊያገኝ ፡ ሮጦ ፡ መድሃኒትን
ሲማትር ፡ ከርሞ ፡ ወንዝ ፡ ሜዳውን
ኋላ ፡ ቆይ ፡ አለ ፡ ሲያይ ፡ እግዚአብሔርን

አዝ፦ ለእኛስ ፡ ከሌላ ፡ ስፍራ ፡ መዳን ፡ ይሆንልናል (፪x)

ዛፉን ፡ ቅጠሉን ፡ እንስሳውን
ኃይለኛ ፡ አዋቂን ፡ ባለጸጋን
ጥበብና ፡ ዕውቀት ፡ ፍልስፍናን
ተስፋ ፡ ያደረግን ፡ ሞትን ፡ ተጐዳን

አዝ፦ ለእኛስ ፡ ከሌላ ፡ ስፍራ ፡ መዳን ፡ ይሆንልናል (፪x)

ኋላ ፡ መለስ ፡ አልን ፡ ሮጠን ፡ ሮጠን
በሙላት ፡ ጋበዝን ፡ ኢየሱስ ፡ ጌታን
ካለሰብንበት ፡ መልስ ፡ አገኘን
ለዘለዓለም ፡ ክብር ፡ ይሁን

አዝ፦ ለእኛስ ፡ ከሌላ ፡ ስፍራ ፡ መዳን ፡ ይሆንልናል (፫x)