ማረኝ ፡ አቤቱ (Maregn Abietu) - ደረጀ ፡ ከበደ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ደረጀ ፡ ከበደ
(Dereje Kebede)

Lyrics.jpg


(4)

መንግሥተ ፡ ሰማይ
(Mengeste Semay)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፸ ፪ (1980)
ቁጥር (Track):

(7)

ርዝመት (Len.): 6:04
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የደረጀ ፡ ከበደ ፡ አልበሞች
(Albums by Dereje Kebede)

አዝ፦ ማረኝ ፡ ጌታ ፡ ሆይ
ማረኝ ፡ አቤቱ ፡ ከመዓቱ (፪x)

እንደሎጥ ፡ አድነኝ ፡ እንደኖህ ፡ አድነኝ
አንደበቴ ፡ ረክሶ ፡ ሰላሜን ፡ ነጠቀኝ
ስንዴነቴን ፡ እንጃ ፡ እንክርዳድ ፡ ብቻ ፡ ነኝ (፪x)

አዝ፦ ማረኝ ፡ ጌታ ፡ ሆይ
ማረኝ ፡ አቤቱ ፡ ከመዓቱ (፪x)

ጌታ ፡ ሆይ ፡ አየሁኝ ፡ ጊዜ ፡ ያሳይ ፡ የለ
ያ ፡ ሁሉ ፡ ግለቴ??? ፡ ተሟጦ ፡ የታለ
ቀኑን ፡ ሙሉ ፡ ልቤ ፡ አንተን ፡ እንዳላለ (፪x)

አዝ፦ ማረኝ ፡ ጌታ ፡ ሆይ
ማረኝ ፡ አቤቱ ፡ ከመዓቱ (፪x)

ቃልህን ፡ ህግህን ፡ እግሬ ፡ ስር ፡ ጥያለሁ
እንደ ፡ ሥጋ ፡ ፈቃዴም ፡ እመላለሳለሁ
ማረኝ ፡ እንደገና ፡ እማጸንሃለሁ (፪x)

አዝ፦ ማረኝ ፡ ጌታ ፡ ሆይ
ማረኝ ፡ አቤቱ ፡ ከመዓቱ (፪x)