እኔስ ፡ በሕይወቴ ፡ ልበርታ (Enies Behiwotie Leberta) - ደረጀ ፡ ከበደ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ደረጀ ፡ ከበደ
(Dereje Kebede)

Lyrics.jpg


(4)

መንግሥተ ፡ ሰማይ
(Mengeste Semay)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፸ ፪ (1980)
ቁጥር (Track):

፲ ፪ (12)

ርዝመት (Len.): 4:44
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የደረጀ ፡ ከበደ ፡ አልበሞች
(Albums by Dereje Kebede)

መሰረቴ ፡ ጠብቆ ፡ ብጓዝ ፡ እወዳለሁ
አለዚያ ፡ በንፋስ ፡ እወዛወዛለሁ
እንደኔማ ፡ እንደሃሳቤ
ድል ፡ ተሞልቶ ፡ ባየሁ ፡ ልቤን (፪x)

አዝ፦ እኔስ ፡ በሕይወቴ ፡ ልበረታ
ምኞቴ ፡ ነው ፡ ጠዋት ፡ ማታ
ለጥሞና ፡ ጊዜ ፡ አጣሁኝ
ዘወትር ፡ በውጊያ ፡ ላይ ፡ እያለሁኝ (፪x)

ማጉረምረምን ፡ ቀርቶ ፡ ምሥጋና ፡ ዘለዓለም
በደስታ ፡ ሰሞን ፡ በስቃይ ፡ ቢሆንም
ይህን ፡ ነበር ፡ የምመኘው
ውጊያ ፡ በዝቶ ፡ የት ፡ ላግኘው (፪x)

አዝ፦ እኔስ ፡ በሕይወቴ ፡ ልበረታ
ምኞቴ ፡ ነው ፡ ጠዋት ፡ ማታ
ለጥሞና ፡ ጊዜ ፡ አጣሁኝ
ዘወትር ፡ በውጊያ ፡ ላይ ፡ እያለሁኝ (፪x)

መብራት ፡ እየበራ ፡ ውስጤ ፡ ገብቶ ፡ ኢየሱስ
ንጹህ ፡ ቦታ ፡ አግኝቶ ፡ ቢኖር ፡ መንፈስ ፡ ቅዱስ
ይህን ፡ ነበር ፡ የምመኘው
ውጊያ ፡ በዝቶ ፡ የት ፡ ላግኘው (፪x)

አዝ፦ እኔስ ፡ በሕይወቴ ፡ ልበረታ
ምኞቴ ፡ ነው ፡ ጠዋት ፡ ማታ
ለጥሞና ፡ ጊዜ ፡ አጣሁኝ
ዘወትር ፡ በውጊያ ፡ ላይ ፡ እያለሁኝ (፪x)

ቅድስና ፡ ሞልቶባቸው ፡ ሁሉም ፡ ብልቶቼ
በኑሮዬ ፡ በጌታ ፡ ግን ፡ ሥጋዬን ፡ ገዝቼ
ልኖር ፡ ነበር ፡ የምመኘው
ውጊያ ፡ በዝቶ ፡ የት ፡ ላግኘው (፪x)

አዝ፦ እኔስ ፡ በሕይወቴ ፡ ልበረታ
ምኞቴ ፡ ነው ፡ ጠዋት ፡ ማታ
ለጥሞና ፡ ጊዜ ፡ አጣሁኝ
ዘወትር ፡ በውጊያ ፡ ላይ ፡ እያለሁኝ (፫x)