እንደ ፡ ሌባ (Ende Lieba) - ደረጀ ፡ ከበደ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ደረጀ ፡ ከበደ
(Dereje Kebede)

Lyrics.jpg


(4)

መንግሥተ ፡ ሰማይ
(Mengeste Semay)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፸ ፪ (1980)
ቁጥር (Track):

፲ ፬ (14)

ርዝመት (Len.): 3:05
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የደረጀ ፡ ከበደ ፡ አልበሞች
(Albums by Dereje Kebede)

አዝ፦ እንደ ፡ ሌባ ፡ እንደ ፡ ወንጀለኛ
ንጹህ ፡ አምላክ ፡ ሆነልን ፡ ስለእኛ
በጨለማ ፡ በድቅድቁ ፡ ሳለን
በእግዚአብሔር ፡ ኢየሱስን ፡ አገኘን (፪x)

እጅግ ፡ ከብዶት ፡ ነበረ ፡ መስቀሉ
አሸክመው ፡ ሲያስጨንቁት ፡ ዋሉ
ለዓለም ፡ ኃጢአት ፡ ኢየሱስ ፡ ተመታ
በመስቀል ፡ ሞት ፡ በእርባን ፡ እንዲፈታ (፪x)

የደሙ ፡ ላብ ፡ አለዋጋ ፡ አይደለም
የጐኑ ፡ ውኃ ፡ ለከንቱ ፡ አልፈሰሰም
ንጹህ ፡ ደሙ ፡ ለእንስሳት ፡ አይደለም
ክቡር ፡ ማንጻት ፡ አለው ፡ ለእኔም ፡ ለአንተም (፪x)

አዝ፦ እንደ ፡ ሌባ ፡ እንደ ፡ ወንጀለኛ
ንጹህ ፡ አምላክ ፡ ሆነልን ፡ ስለእኛ
በጨለማ ፡ በድቅድቁ ፡ ሳለን
በእግዚአብሔር ፡ ኢየሱስን ፡ አገኘን (፪x)