ድንቅ ፡ ሥራ (Denq Sera) - ደረጀ ፡ ከበደ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ደረጀ ፡ ከበደ
(Dereje Kebede)

Lyrics.jpg


(4)

መንግሥተ ፡ ሰማይ
(Mengeste Semay)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፸ ፪ (1980)
ቁጥር (Track):

(1)

ርዝመት (Len.): 2:53
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የደረጀ ፡ ከበደ ፡ አልበሞች
(Albums by Dereje Kebede)

ኮረብታውን ፡ ወጥቼ ፡ እፎይ ፡ አልኩኝ
ድንቅ ፡ የሆኑ ፡ ፍጥረታትን ፡ እያየሁኝ
ብቻዬን ፡ ነኝ ፡ ለማለት ፡ አልደፈርኩም
በዙሪያዬ ፡ አጫዋች ፡ አላጣሁም

አዝ፦ ድንቅ ፡ ስራ ፡ የአምላክ ፡ ስራ ፡ አይወራ
ድንቅ ፡ ስራ ፡ የአምላክ ፡ ስራ ፡ አይወራ

ቀስ ፡ እያልኩኝ ፡ ቀጠልኩኝ ፡ እርምጃዬን
አቤት ፡ ወፎች ፡ ከበውኛል ፡ ዙሪያዬን
ልዩ ፡ ልዩ ፡ ቀለም ፡ ለብሰው ፡ ሲጫወቱ
ደስ ፡ ያሰኛል ፡ የአምላክ ፡ ጥበብ ፡ መሰረቱ

አዝ፦ ድንቅ ፡ ስራ ፡ የአምላክ ፡ ስራ ፡ አይወራ
ድንቅ ፡ ስራ ፡ የአምላክ ፡ ስራ ፡ አይወራ

ሽው ፡ እያለ ፡ በሚያዝናናኝ ፡ ነፋስ ፡ ደግሞ
ሲወዛወዝ ፡ የ. (1) . ፡ አንገት ፡ ዘሞ
አንዴ ፡ ቀና ፡ አንዴ ፡ ጐንበስ ፡ አቤት ፡ . (2) .
እንዴት ፡ ሰራው ፡ ታላቅ ፡ ጌታስ ፡ ያሰኛል

አዝ፦ ድንቅ ፡ ስራ ፡ የአምላክ ፡ ስራ ፡ አይወራ
ድንቅ ፡ ስራ ፡ የአምላክ ፡ ስራ ፡ አይወራ

የአበቦቹ ፡ መዓዛ ፡ እያወደኝ
ልዩ ፡ ቃና ፡ ለአካላቴ ፡ እየሰጠኝ
በአምላክ ፡ እጆች ፡ በተሰሩት ፡ ተደንቄ
ተመለስኩኝ ፡ ወደ ፡ ቤቴ ፡ ብዙ ፡ አውቄ

አዝ፦ ድንቅ ፡ ስራ ፡ የአምላክ ፡ ስራ ፡ አይወራ
ድንቅ ፡ ስራ ፡ የአምላክ ፡ ስራ ፡ አይወራ