From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
አዝ፦ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ከሞት ፡ ሕይወት ፡ ይመረጣል
ብልህ ፡ ሰው ፡ ነፍሱን ፡ ያድናል
በስምህ ፡ ትዕዛዝ ፡ ስር ፡ ያድራል
በልቡ ፡ አንተን ፡ ፈላጊ
ስምህን ፡ ጠሪ ፡ ይባረካል
በኑሮ ፡ የሚያስቀድምህ
የደስታን ፡ ካባን ፡ ይደርባል
ከእርኩሰት ፡ ታርቀዋለህ
በልቡ ፡ ዙፋን ፡ ላይ ፡ ነግሰህ
ሰላምን ፡ በውስጡ ፡ አኑሮ
ይጓዛል ፡ ደስታን ፡ ጨምሮ
አዝ፦ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ከሞት ፡ ሕይወት ፡ ይመረጣል
ብልህ ፡ ሰው ፡ ነፍሱን ፡ ያድናል
በስምህ ፡ ትዕዛዝ ፡ ስር ፡ ያድራል
ከኋለኛው ፡ ሃዘን ፡ ይልቅ
የአሁኑን ፡ ጉስቁልና ፡ መርጦ
ጊዜያዊውን ፡ ተድላ ፡ ንቆ
ነፍሱን ፡ ከሥጋው ፡ ያየ ፡ አብልጦ
ብልህ ፡ ነው ፡ ጠቢብ ፡ አዋቂ
የሰማይ ፡ ሃገር ፡ ዘላቂ
ዘለዓለም ፡ እረፍትን ፡ አይቷል
ለተስፋው ፡ ምድር ፡ ተመርጧል
አዝ፦ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ከሞት ፡ ሕይወት ፡ ይመረጣል
ብልህ ፡ ሰው ፡ ነፍሱን ፡ ያድናል
በስምህ ፡ ትዕዛዝ ፡ ስር ፡ ያድራል
በለመለመ ፡ መስክ ፡ አድሮ
የጠራ ፡ ምንጭ ፡ ውኃ ፡ ጠጥቶ
በአምላኩ ፡ እንክብካቤ ፡ አድርጐ
መጓዙን ፡ የሰው ፡ ልጅ ፡ አጥላልቶ
ከስታለች ፡ ተርባ ፡ ነፍሱ
ታውኳል ፡ ሥጋ ፡ መንፈሱ
ይመለስ ፡ ሚወድ ፡ ይመለስ
ሳይወድቅ ፡ ጉልበቱ ፡ ሳይፈር
አዝ፦ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ከሞት ፡ ሕይወት ፡ ይመረጣል
ብልህ ፡ ሰው ፡ ነፍሱን ፡ ያድናል
በስምህ ፡ ትዕዛዝ ፡ ስር ፡ ያድራል (፬x)
|