ተማርኬለሁ (Temarikyalew) - ደረጀ ከበደ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ደረጀ ከበደ
(Dereje Kebede)

Lyrics.jpg


(7)

ሂወት ይሻለናል
(Hiweot Yshalenal)

ቁጥር (Track):

(1)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የደረጀ ከበደ ፡ አልበሞች
(Albums by Dereje Kebede)

አታገለኝ ትግል ከማልችለው ጋራ
አቅሜን አለማወቅ አጉል ስንጠራራ
ኤልሻዳይ ከሰማይ ወደታች እያየኝ
ትጥቄ ላልቶ ስወድቅ አዝኖ ሰበሰበኝ

አይኔን አንስቸ ጨፍኘ እንዳላይህ
በአጥንቴ ቀረሁ መነመንኩኝ ልጅህ
የምድረ በዳ ኑሮ ይበቃኛል
እጆቸን ላንሳ
ዛሬስ ማርከኸኛል
ተማርኬያልሁ

ወደ ምስራቅ ሲለኝ ምዕራቡን ስከተል
ያከለለልኝን ቅጥር ጥሸ ስዘል
ብዙ ተገጣጠብኩ ጠባሳ ብቻ ንኝ
ይቅርታው ብዙ ነው
ምህረቱ ያስታመኝ

አይኔን አንስቸ ጨፍኘ እንዳላይህ
በአጥንቴ ቀረሁ መነመንኩኝ ልጅህ
የምድረ በዳ ኑሮ ይበቃኛል
እጆቸን ላንሳ
ዛሬስ ማርከኸኛል
ተማርኬያልሁ (2x)

የዘላለም ቁጡ እንዳሆን በኔ ላይ
እግዚአብሄር በልጁ ቀደሰኝ ከሰማይ
በእግሮቹ ስር ሆኘ ትዛዙን ፈፅሜ
መኖር ነው ምኞቴ በቀረው ዘመኔ

አይኔን አንስቸ ጨፍኘ እንዳላይህ
በአጥንቴ ቀረሁ መነመንኩኝ ልጅህ
የምድረ በዳ ኑሮ ይበቃኛል
እጆቸን ላንሳ
ዛሬስ ማርከኸኛል
ተማርኬያልሁ