From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
አዝ፦ የትግሉን ፡ ምዕራፍ ፡ ተወጥተን
ሜዳ ፡ ተራራውን ፡ ዘልቀን
ሳንለያይ ፡ በአንድ ፡ ሆነን
ከወንዙ ፡ ማዶ ፡ እንገናኛለን (፪x)
ተሰምቶ ፡ የማያውቅ ፡ ድል ፡ ሲሰማ
ሲሰበሰብ ፡ ባለመንፈስ ፡ አድማ
ለማመስገን ፡ በአንድ ፡ ሆነን
ከወንዙ ፡ ማዶ ፡ እንዘምራለን
አዝ፦ የትግሉን ፡ ምዕራፍ ፡ ተወጥተን
ሜዳ ፡ ተራራውን ፡ ዘልቀን
ሳንለያይ ፡ በአንድ ፡ ሆነን
ከወንዙ ፡ ማዶ ፡ እንገናኛለን (፪x)
በለምለሙ ፡ ስፍራ ፡ ለመኖር ፡ አብረን
ሸለቆውን ፡ አልፈን ፡ ወንዙን ፡ ተሻግረን
ልንኖር ፡ በደስታ ፡ ለዘለዓለም
አርፈን ፡ ከስቃይ ፡ ከዚህ ፡ ዓለም
አዝ፦ የትግሉን ፡ ምዕራፍ ፡ ተወጥተን
ሜዳ ፡ ተራራውን ፡ ዘልቀን
ሳንለያይ ፡ በአንድ ፡ ሆነን
ከወንዙ ፡ ማዶ ፡ እንገናኛለን (፪x)
ዙፋኑን ፡ በሰፊው ፡ ካንጣለለው
በረከት ፡ ፀጋና ፡ ክብርም ፡ ካለው
ጌታችን ፡ ዘንድ ፡ እንኖራለን
የትግሉን ፡ ምዕራፍ ፡ ተወጥተን
አዝ፦ የትግሉን ፡ ምዕራፍ ፡ ተወጥተን
ሜዳ ፡ ተራራውን ፡ ዘልቀን
ሳንለያይ ፡ በአንድ ፡ ሆነን
ከወንዙ ፡ ማዶ ፡ እንገናኛለን (፪x)
|