ያምላኬ ፡ ቃል ፡ አያረጅም (Yamlakie Qal Ayarejem) - ስዩም ገብረየስ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ስዩም ገብረየስ
(Seyoum Geberyase)

Lyrics.jpg


(Volume)

ስብስብ
(Collection 2)

ቁጥር (Track):

(1)

ርዝመት (Len.): 3:04
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የስዩም ገብረየስ ፡ አልበሞች
(Albums by Seyoum Geberyase)

አዝ፦ ያምላኬ ፡ ቃል ፡ አያረጅም
የኢየሱስ ፡ ቃል ፡ አያረጅም
ዘለዓለም ፡ ይኖራል ፡ እያበራ
ከሚያምኑት ፡ ጋራ (፪x)

ተስፋ ፡ ስቆርጥ ፡ ያጽናናኛል
አቅፎ ፡ ደግፎ ፡ ያኖረኛል
በደሙ ፡ አጥቦ ፡ አንጽቶኛል
ኮብልዬ ፡ እንዳልሄድ ፡ ይጠብቀናል

አዝ፦ ያምላኬ ፡ ቃል ፡ አያረጅም
የኢየሱስ ፡ ቃል ፡ አያረጅም
ዘለዓለም ፡ ይኖራል ፡ እያበራ
ከሚያምኑት ፡ ጋራ (፪x)

በዓለም ፡ ጉዞዬ ፡ ይደግፈኛል
ፍፁም ፡ ላይተወኝ ፡ ተስፋ ፡ ሰጥቶኛል
አልተወውም ፡ አይተወኝም
የኢየሱሴ ፡ ነኝ ፡ እስከዘለዓለም

አዝ፦ ያምላኬ ፡ ቃል ፡ አያረጅም
የኢየሱስ ፡ ቃል ፡ አያረጅም
ዘለዓለም ፡ ይኖራል ፡ እያበራ
ከሚያምኑት ፡ ጋራ (፪x)

ሥጋዬ ፡ ደክሞ ፡ ነፍሴ ፡ ተጨንቃ ፡ ስታንቀላፋ
የአምላኬ ፡ ቃል ፡ ያነቃኛል ፡ በሰጠኝ ፡ ተስፋ

ልጁ ፡ ሆኛለሁ ፡ ዳግም ፡ ወልዶኛል
ኃጢአቴን ፡ ሁሉ ፡ ደምስሶልኛል
ጌታዬ ፡ አቅፎኝ ፡ በእርሱ ፡ ስር ፡ ካለሁ
ብርሃን ፡ እያየሁ ፡ እጓዛለሁ

አዝ፦ ያምላኬ ፡ ቃል ፡ አያረጅም
የኢየሱስ ፡ ቃል ፡ አያረጅም
ዘለዓለም ፡ ይኖራል ፡ እያበራ
ከሚያምኑት ፡ ጋራ (፪x)
ከሚያምኑት ፡ ጋራ