From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
አዝ፦ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ጨርቅህን ፡ ይዤ ፡ እማፀናለሁ
ከአንተ ፡ ወዴት ፡ ከቶ ፡ እሄዳለሁ
ደጃፍህ ፡ ብኖር ፡ ተጥዬ
ክብሬ ፡ ነው ፡ ለእኔ ፡ ተስፋዬ
ድካሜን ፡ አውቃለሁ ፡ ኃጢያት ፡ ሲያሸንፈኝ
ያም ፡ ቢሆን ፡ ጨርቅህን ፡ ማንም ፡ አያስጥለኝ
ማንም ፡ አያስጥለኝ
የአመፃዬ ፡ ክምር ፡ ቢያስቆጣህም ፡ በጣም
አንተው ፡ እስክትምረኝ ፡ ከቤትህ ፡ አልወጣም
ከቤትህ ፡ አልወጣም
አዝ፦ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ጨርቅህን ፡ ይዤ ፡ እማፀናለሁ
ከአንተ ፡ ወዴት ፡ ከቶ ፡ እሄዳለሁ
ደጃፍህ ፡ ብኖር ፡ ተጥዬ
ክብሬ ፡ ነው ፡ ለእኔ ፡ ተስፋዬ
ፍሬ ፡ አልባ ፡ ንሰሃ ፡ ነጋ ፡ ጠባ ፡ ማረኝ
በፊትህ ፡ እንዳልቆይ ፡ እጅግ ፡ አሳፈረኝ
እጅግ ፡ አሳፈረኝ
አመጻዬ ፡ በዝቶ ፡ ጭቃ ፡ ባላቁጥም
ደጅህ ፡ እሞታለሁ ፡ ተስፋዬን ፡ አልቆርጥም
ተስፋዬን ፡ አልቆርጥም
አዝ፦ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ጨርቅህን ፡ ይዤ ፡ እማፀናለሁ
ከአንተ ፡ ወዴት ፡ ከቶ ፡ እሄዳለሁ
ደጃፍህ ፡ ብኖር ፡ ተጥዬ
ክብሬ ፡ ነው ፡ ለእኔ ፡ ተስፋዬ
የነፍሴን ፡ ውሳኔ ፡ አንተው ፡ ታውቀዋለህ
እንደምወድህም ፡ ውስጤን ፡ ታየዋለህ
ውስጤን ፡ ታየዋለህ
ከልጅነት ፡ ወራት ፡ ጀምሮ ፡ አውቅሃለሁ
እንዳንተ ፡ ቸር ፡ ወዳጅ ፡ ወዴት ፡ አገኛለሁ
ወዴት አገኛለሁ
አዝ፦ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ጨርቅህን ፡ ይዤ ፡ እማፀናለሁ
ከአንተ ፡ ወዴት ፡ ከቶ ፡ እሄዳለሁ
ደጃፍህ ፡ ብኖር ፡ ተጥዬ
ክብሬ ፡ ነው ፡ ለእኔ ፡ ተስፋዬ
ለህይወቴ ፡ ሰላም ፡ ለልቤ ፡ ፀጥታ
ዘለአለም ፡ ገዥዬ ፡ አንተ ፡ ብቻ ፡ ጌታ
አንተ ፡ ብቻ ፡ ጌታ
ግራ ፡ ቀኝም ፡ አልል ፡ ነፍሴንም ፡ አልሸጣት
ከአንተ ፡ ተለይታ ፡ አወይ ፡ ትርጉም ፡ የላት
አወይ ፡ ትርጉም ፡ የላት
አዝ፦ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ጨርቅህን ፡ ይዤ ፡ እማፀናለሁ
ከአንተ ፡ ወዴት ፡ ከቶ ፡ እሄዳለሁ
ደጃፍህ ፡ ብኖር ፡ ተጥዬ
ክብሬ ፡ ነው ፡ ለእኔ ፡ ተስፋዬ
|