ወንዙ ፡ ከፊት ፡ ሲታይህ (Wenzu Kefit Sitayeh) - ደረጀ ፡ ከበደ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ደረጀ ፡ ከበደ
(Dereje Kebede)

Dereje Kebede Esp.jpg

ልዩ ፡ እትም
(Esp)

ስብስብ
(Collection)

ቁጥር (Track):

(6)

ርዝመት (Len.): 2:04
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የደረጀ ፡ ከበደ ፡ አልበሞች
(Albums by Dereje Kebede)

አዝ፦ ወንዙ ፡ ከፊት ፡ ሲታይህ
ቢመስልህ ፡ የሚውጥህ
ታምነህ ፡ ጉዞህን ፡ ቀጥል
ጌታ ፡ ይመራሃል

የማዕበሉ ፡ ጌታ ፡ ቀድሞሃል
ተከተለኝ ፡ አይዞህ ፡ ይልሃል
ቀና ፡ ነው ፡ መንገዱ ፡ ተጽናና
የናዝሬቱ ፡ ኢየሱስ ፡ አለና

አዝ፦ ወንዙ ፡ ከፊት ፡ ሲታይህ
ቢመስልህ ፡ የሚውጥህ
ታምነህ ፡ ጉዞህን ፡ ቀጥል
ጌታ ፡ ይመራሃል

ባሕሩ ፡ አፍ ፡ ለአፍ ፡ ሞልቶ
ወጀብ ፡ ሲያናውጠው ፡ በርትቶ
ሰንጥቀህ ፡ ማለፍን ፡ ብትፈራ
ቶሎ ፡ ብለህ ፡ ጌታህን ፡ ጥራ

አዝ፦ ወንዙ ፡ ከፊት ፡ ሲታይህ
ቢመስልህ ፡ የሚውጥህ
ታምነህ ፡ ጉዞህን ፡ ቀጥል
ጌታ ፡ ይመራሃል

ሁሉንም ፡ በቃሉ ፡ ያዘዋል
ፍጥረትም ፡ ለእርሱ ፡ ይታዘዛል
ሁሉን ፡ ቻይ ፡ ጌታ ፡ አለ ፡ ከፊትህ
ጠላት ፡ ሲረፈረፍ ፡ ታያለህ

አዝ፦ ወንዙ ፡ ከፊት ፡ ሲታይህ
ቢመስልህ ፡ የሚውጥህ
ታምነህ ፡ ጉዞህን ፡ ቀጥል
ጌታ ፡ ይመራሃል

በባሕሩ ፡ ጉዞ ፡ ብትዝልም
አይዞህ ፡ መንገድ ፡ ላይ ፡ አትቀርም
ጌታህ ፡ አጠገብህ ፡ አለና
እርዳኝ ፡ በለው ፡ ጠጋ ፡ በልና

አዝ፦ ወንዙ ፡ ከፊት ፡ ሲታይህ
ቢመስልህ ፡ የሚውጥህ
ታምነህ ፡ ጉዞህን ፡ ቀጥል
ጌታ ፡ ይመራሃል (፪x)