ተራመድ (Teramed) - ደረጀ ፡ ከበደ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ደረጀ ፡ ከበደ
(Dereje Kebede)

Dereje Kebede Esp.jpg

ልዩ ፡ እትም
(Esp)

ስብስብ
(Collection)

ቁጥር (Track):

(20)

ርዝመት (Len.): 2:08
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የደረጀ ፡ ከበደ ፡ አልበሞች
(Albums by Dereje Kebede)

አዝ፦ ተራመድ ፡ በርታ ፡ በርታ
ጉዞህንም ፡ ፈጽም
ሕይወትንም ፡ አድን

የመከራ ፡ ጉም ፡ በላይ ፡ ቢያንዣብብ
አለና ፡ ኢየሱስ ፡ ፍፁም ፡ አታስብ
ቢመስልህ ፡ ጉዞ ፡ ፍፁም ፡ ተራራ
ደጋፊ ፡ አለህ ፡ ፍፁም ፡ አትፍራ

አዝ፦ ተራመድ ፡ በርታ ፡ በርታ
ጉዞህንም ፡ ፈጽም
ሕይወትህንም ፡ አድን

በኃጢአት ፡ ቁስል ፡ ብትማቅቅም
በሱ ፡ ከታመንክ ፡ ፍፁም ፡ አትወድቅም
ስለሚመለስ ፡ ጌታ ፡ ከሰማይ
መብራትህ ፡ ይብራ ፡ ለዓለምም ፡ ይታይ

አዝ፦ ተራመድ ፡ በርታ ፡ በርታ
ጉዞህንም ፡ ፈጽም
ሕይወትህንም ፡ አድን

አትሞኝ ፡ ከቶ ፡ በዓለም ፡ ደስታ
ስለማታገኝ ፡ የሕይወት ፡ እርካታ
መቅረዝህ ፡ ይብራ ፡ ቁም ፡ ተዘጋጅተህ
ጌታ ፡ ሲመለስ ፡ ትነጠቃለህ

አዝ፦ ተራመድ ፡ በርታ ፡ በርታ
ጉዞህንም ፡ ፈጽም
ሕይወትህንም ፡ አድን

ቋሚ ፡ ጓደኛ ፡ ስላለህ ፡ ኢየሱስ
በእምነት ፡ ተጋደል ፡ በተስፋ ፡ ገስግስ
ዓለምን ፡ አትይ ፡ ማብለጭለጯንም
ተስፋ ፡ ከመቁረጥ ፡ አታድንህም

አዝ፦ ተራመድ ፡ በርታ ፡ በርታ
ጉዞህንም ፡ ፈጽም
ሕይወትህንም ፡ አድን (፪x)

ሕይወትህንም ፡ አድን