ከባሕር ፡ ሞገድ (Kebaher Modeg) - ደረጀ ፡ ከበደ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ደረጀ ፡ ከበደ
(Dereje Kebede)

Dereje Kebede Esp.jpg

ልዩ ፡ እትም
(Esp)

ስብስብ
(Collection)

ቁጥር (Track):

፲ ፬ (14)

ርዝመት (Len.): 2:03
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የደረጀ ፡ ከበደ ፡ አልበሞች
(Albums by Dereje Kebede)

አክሊሌን ፡ በደምህ ፡ ልሸሽገው
የሰው ፡ ልጅ ፡ ጠላት ፡ ሰይጣን ፡ እንዳይሰርቀው
መፈታተኑን ፡ አላቋረጠም
አንተ ፡ እስክትመጣ ፡ በክብር ፡ ወደዚች ፡ ዓለም

ከባሕር ፡ ሞገድ ፡ ከአየር ፡ ነጐድጓድ
በሚበልጥ ፡ ኃይልህ ፡ ኢየሱስ ፡ የእግዚአብሔር ፡ ልጅ ፡ ወልድ
አጥበኸኝ ፡ እኔን ፡ ድኛለሁ ፡ ጌታ
ለአክሊልህ ፡ ያብቃኝ ፡ ኢየሱስ ፡ እንዳልረታ

ጠበቃዬና ፡ አክሊሌን ፡ ይዘህ
በመርከብህ ፡ ውስጥ ፡ ልግባ ፡ እኔም ፡ እንደ ፡ ኖህ
ጐልማሳነቴን ፡ ሩጫዬን ፡ በቃኝ
አክሊሌን ፡ ከአንተ ፡ ኢየሱስ ፡ ለመውሰድ ፡ አብቃኝ

ከባሕር ፡ ሞገድ ፡ ከአየር ፡ ነጐድጓድ
በሚበልጥ ፡ ኃይልህ ፡ ኢየሱስ ፡ የእግዚአብሔር ፡ ልጅ ፡ ወልድ
አጥበኸኝ ፡ እኔን ፡ ድኛለሁ ፡ ጌታ
ላክሊልህ ፡ ያብቃኝ ፡ ኢየሱስ ፡ እንዳልረታ