ካልባረከኝ (Kalbarekegn) - ደረጀ ፡ ከበደ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ደረጀ ፡ ከበደ
(Dereje Kebede)

Dereje Kebede Esp.jpg

ልዩ ፡ እትም
(Esp)

ስብስብ
(Collection)

ቁጥር (Track):

፲ ፫ (13)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የደረጀ ፡ ከበደ ፡ አልበሞች
(Albums by Dereje Kebede)

ለብቻዬ ፡ ልኖር ፡ ፈቃድህ ፡ ከሆነ
ሌላው ፡ አይገደኝም ፡ ሕይወቴ ፡ ከዳኔ
ሲሆን ፡ እስከንጋት ፡ ልታገልህና
ስደደኝ ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ሕይወቴን ፡ ባርክና

አዝ፦ ካልባረከኝ ፡ አለቅህም (፪x)
ካልባረከኝ ፡ አለቅህም (፪x)

ከመምበርከክ ፡ ብዛት ፡ በጸሎት ፡ ትግል
ፈቃድህ ፡ ከሆነ ፡ ጉልበቴ ፡ ይዛል
እያነከስኩ ፡ ይሁን ፡ እከተልሃለሁ
እጅህን ፡ ዘርጋብኝ ፡ በረከት ፡ እሻለሁ

አዝ፦ ካልባረከኝ ፡ አለቅህም (፪x)

ሊነጋ ፡ ሲጀምር ፡ ሰማዩም ፡ ሲቀላ
ወደዚህ ፡ እሄዳለሁ ፡ ነፍሴ ፡ እንዲህ ፡ ዝላ
ሕይወቴን ፡ ብቻ ፡ ባርክ ፡ ሌላ ፡ አልመኝም
ሥም ፡ እንደው ፡ ቀሪ ፡ ነው ፡ ሥም ፡ አያድነኝም

አዝ፦ ካልባረከኝ ፡ አለቅህም (፪x)
ካልባረከኝ ፡ አለቅህም (፪x)

እንደ ፡ ያዕቆብ ፡ ዛሬ ፡ ጩኸቴን ፡ ስማና
ስደደኝ ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ሕይወቴን ፡ ባርክና
ፈቃድህ ፡ ከሆነ ፡ ስሜንም ፡ ለውጠው
ሰው ፡ እንዳለው ፡ ሳይሆን ፡ አንተ ፡ እንደ ፡ ወደድከው

አዝ፦ ካልባረከኝ ፡ አለቅህም (፪x)
ካልባረከኝ ፡ አለቅህም (፪x)