ግሩም ፡ ነው ፡ ድንቅ ፡ ነው (Girum New Denq New) - ደረጀ ፡ ከበደ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ደረጀ ፡ ከበደ
(Dereje Kebede)

Lyrics.jpg


()

ስብስብ
(Collection)

ቁጥር (Track):

(10)

ርዝመት (Len.): 2:53
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የደረጀ ፡ ከበደ ፡ አልበሞች
(Albums by Dereje Kebede)

አዝ፦ ግሩም ፡ ነው ፡ ድንቅ ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ ሲሰራ
አየነው ፡ ምርኮው ፡ ላይ ፡ ግርማው ፡ ሲያበራ
የኃጢአት ፡ መጋረጃን ፡ በደሙ ፡ ቀደደ
ከሳሻችን ፡ አፍሮ ፡ ወድቆ ፡ ሰገደ

ይከሰን ፡ የነበረው ፡ የእዳ ፡ ጽሕፈት
በደሙ ፡ ተደምስሷል ፡ በጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ሞት
ቀንበራችን ፡ ተሰብሮ ፡ አርነት ፡ ወጥተናል
ጠላቶች ፡ የነበርነው ፡ በፀጋው ፡ ቀርበናል

አዝ፦ ግሩም ፡ ነው ፡ ድንቅ ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ ሲሰራ
አየነው ፡ ምርኮው ፡ ላይ ፡ ግርማው ፡ ሲያበራ
የኃጢአት ፡ መጋረጃን ፡ በደሙ ፡ ቀደደ
ከሳሻችን ፡ አፍሮ ፡ ወድቆ ፡ ሰገደ

ከድቅድቅ ፡ ጨለማ ፡ ወደሚደነቅ ፡ ብርሃን
በጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ሥራ ፡ እግዚአብሔር ፡ ጠራን
ተስፋችን ፡ ያከተመ ፡ ደካሞች ፡ ሳለን
በዘመኑ ፡ ፍፃሜ ፡ በልጁ ፡ ዋጀን

አዝ፦ ግሩም ፡ ነው ፡ ድንቅ ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ ሲሰራ
አየነው ፡ ምርኮው ፡ ላይ ፡ ግርማው ፡ ሲያበራ
የኃጢአት ፡ መጋረጃን ፡ በደሙ ፡ ቀደደ
ከሳሻችን ፡ አፍሮ ፡ ወድቆ ፡ ሰገደ

አእላፋት ፡ መላዕክት ፡ አገልጋይ ፡ ሳያንሰው
ስለጠፋው ፡ የሰው ፡ ልጅ ፡ አንድ ፡ ልጁን ፡ ሰዋው
በኃጢአት ፡ ረግረግ ፡ ውስጥ ፡ ሰጥመን ፡ ለጠፋነው
ሊታደገን ፡ ወደደ ፡ ጭንቀታችን ፡ ተሰማው

አዝ፦ ግሩም ፡ ነው ፡ ድንቅ ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ ሲሰራ
አየነው ፡ ምርኮው ፡ ላይ ፡ ግርማው ፡ ሲያበራ
የኃጢአት ፡ መጋረጃን ፡ በደሙ ፡ ቀደደ
ከሳሻችን ፡ አፍሮ ፡ ወድቆ ፡ ሰገደ

መንገድ ፡ ተዘጋጀልን ፡ ግዛቱ ፡ ልንገባ
የከበደን ፡ ቀንበር ፡ ሆኗል ፡ እንደ ፡ ገለባ
እንራመዳለን ፡ ሸክም ፡ ቀሎናልና
ዕረፍትን ፡ ስላገኘን ፡ ሆነን ፡ በምሥጋና

አዝ፦ ግሩም ፡ ነው ፡ ድንቅ ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ ሲሰራ
አየነው ፡ ምርኮው ፡ ላይ ፡ ግርማው ፡ ሲያበራ
የኃጢአት ፡ መጋረጃን ፡ በደሙ ፡ ቀደደ
ከሳሻችን ፡ አፍሮ ፡ ወድቆ ፡ ሰገደ